በዮሴፍ ከፈለኝ
“
የማን ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ ሰራተኛ
በመሆኑና ሰርቶ ለውጤት መብቃትን
ለተጨዋቾች ያሳየ በመሆኑ ከሜሲ ይልቅ
ለሮናልዶ ቅድሚያ እሰጣለሁ” የሚለው
የዋሊያዎቹ የነገ ተስፋ የፈረሰኞቹ ወጣቱ
ኃይል አቤል ያለው ነው፡፡ ከዮሴፍ ከፈለኝ
ጋር በነበረው ቆይታ መሪነቱን መረከባችን
የሚጠበቅ ነው፡፡ ሊጉን አሸንፈን በሻምፒዮንስ
ሊግ የመካፈል ህልማችንን የምናሳካበት
አመት ነው ሲል ለሀትሪክ ተናግሯል፡፡
አቤልና ዮሴፍ ያደረጉት አጠር ያለ ቆይታ
ይህን ይመስላል፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ቡና መሸነፍና
የእናንተ ማሸነፍን ተከትሎ የሊጉ መሪ
ሆናችሁ… ምን ተሰማችሁ?
አቤል፡- የተለየ ስሜት አልተሰማንም….
የጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ቀሪ አንድ ጨዋታ አለን
በማሸነፍ ልዩነቱን ለማስፋት እንሞክራለን፡፡
ቡድናችን ገና እየተሰራ ያለ ቡድን እንደመሆኑ
ለወደፊቱ ጠንካራ ሆኖ ከዚህ የተሻለ ብቃት
እንደሚኖረን አልጠራጠርም፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- ጊዮርጊስ አንዴ ይምራ እንጂ
እንዴት ዋንጫ ማሸነፍ እንዳለበት ያውቃል
የሚሉ አሉ… ትስማማለህ?
አቤል፡- እውነትኮ ነው ይሄ ባህሪ
ጊዮርጊስን ሳልቀላቀልም አውቀው ነበር
አንዴ ከመራ ጊዮርጊስ አስቸጋሪ እንደሚሆን
ይታወቃል፡፡ ይሄ በዚህ አመትም ይደገማል
ባይ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ምርጥ አቋሜ ላይ ነኝ ማለት
ትችላለህ?
አቤል፡- ኧረ አይደለም፡፡ ጠንክሬ
እየሰራሁ በመሆኑ ከዚህ በላይ የተሻለው
አቤል በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ይታያል፡
፡ እረፍትና መተኛት እወዳለሁ ይሄ ደግሞ
ለተጨዋች ወሳኝ ነው ልምምዴን ጠንክር
እሰራለሁ የተሻለ ጊዜ ወደፊትም ይኖረኛል፡፡
ሀትሪክ፡- ኮከብ ጎል አግቢ የሆን ህልሙ
አለህ?
አቤል፡- የርሱ ዘመን ወደፊት ይመጣል
ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ አሁን ግን ቅዱስ
ጊዮርጊስን ስለመጥቀም እንጂ ኮከብ ጎል
አግቢ ስለመሆን አስቤ አላውቅም ከዚህ
ይልቅ ሳላሀዲን ሰይድ ልምዱና አቅሙ
ስላለው በኮከብ ጎል አግቢነቱ ይሳካለታል ብዬ
አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡- እንደ ቡድን ጫና አለባችሁ?
አቤል፡- ጫና የለብንም እንደ ጊዮርጊስ
ተጫዋችነታችን ግን ሁሉንም ጨዋታ
የማሸነፍ ግዴታ አለብን፡፡
ሀትሪክ፡- በግልስ አቤል ላይ ጫና አለ?
አቤል፡- በፍፁም ጫና የለብኝም…
ደጋፊውም ከጎኔ ሆኖ ስለሚያበረታታኝ ጫና
የለብኝም በቡድኑና በእስካሁኑ ደስተኛ ነኝ
በዚህ አጋጣሚ ደጋፊውን አመሰግናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በቡድኑ ውስጥ የተለየ የሆነብህ
ነገር አለ?
አቤል፡- የማሸነፍ ጉጉት…. ፕሪሚየር
ሊጉን አሸንፈን ወደ አፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ
የማለፍ ጉጉት አለብን፡፡
ሀትሪክ፡- የዋንጫ አሸናፊ ነን ለዚህ
ጥርጥር የለም የሚሉ ድምጾች እየተሰሙ
ነው… እናንተ ጋር ይሄ ስሜት አለ?
አቤል፡- ጨዋታው ገና ነው ነገር ግን
ቡድናችን የዋንጫ ቲም ነው ከፊታችን
ያሉትን ጨዋታዎች እያሸነፍን ሄደን
ዋንጫውን እንደምንወስድ እምነቱ አለን፡፡
ሀትሪክ፡- በክልል ማሸነፋችሁ
ጥንካሬያችሁን አያሳይም?
አቤል፡- ይሄማ ምን ጥርጥር አለው…
ጠንካራ ሊግ እንደመሆኑ ፉክክሩ ጨምሯል
በክልል ማሸነፍ ከባድ ቢሆንም ክልል ላይ
እያሸነፍን መሆኑ የዋንጫ ቡድን መሆናችንን
ያሳያል፡፡
ሀትሪክ፡- ለደጋፊያዎቻችሁ የምትለው
ነገር አለ?
አቤል፡- በክልልም ሆነ በአዲስ አበባ
ጨዋታ ባለብን ቦታ ሁሉ እየተገኙ
ደግፈውናል ዋንጫ ይገባቸዋል ለድጋፋቸውም
ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ በቀጣይ ጨዋታዎች
ከፈጣሪ ጋር የሚያቆመን አይኖርም ብዬ
አምናለው የሁልጊዜ ድጋፋቸው አይለየን
ማለት እፈልጋለው።