አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2-1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የሀዋሳ ቆይታዉንን በድል ቋጭቷል !!
በተመጣጣኝ የጨዋታ ድባብ የሁለቱም ክለቦች ጨዋታ መካሄድ የጀመረ ሲሆን በአንፃሩ ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ በሁለቱም በኩል ተመልክተናል።
ለጎል የቀረቡ ኳሶች ሙከራ በሁለቱም ቡድን በኩል ሳይደረግ ጨዋታዉ ያለ ግብ እስከ መጀመሪያዉ አጋማሽ መገባደጃ ድረስ ቢደርስም በ30ኛዉ ደቂቃ ለድሬዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ጎል ቻርለስ ሙሰጊ አስቆጥሮ ጨዋታዉ ወደ 1-0 ሊያመራ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከጎሏ መቆጠር በኋላ ጨዋታዉ በቀድሞ መንፈሱ እንደተቀዛቀዘ የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ ጎል ሳይስተናገድበት በድሬዳዋ ከነማ 1-0 መሪነት የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል።
ከእረፍት መልስ አዳማ ከነማዎች በተሻለ የጨዋታ መንፈስ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን በዳዋ ሆጤሳ እና በዮሴፍ ታረቀኝ በኩል ተደጋጋሚ ለጎል የቀረቡ ኳሶችን ሲሞክሩ ነበር።
ወደ ድሬዎች የግብ ክልል አዘንብለዉ ተደጋጋሚ ሙከራ እያደረጉ ሲጫወቱ የነበሩት አዳማ ከነማዎች አቻ መሆን የቻሉበትን ጎል በ59ኛዉ ደቂቃ በአቡበክር ወንድሙ በኩል ሊያስቆጥሩ ችለዋል።
ጎሏ ከተቆጠረች በኋላ አዳማ ከነማዎች ይበልጥ ወኔ የተላበሰ አጨዋወት በሜዳ ሲያስመለክቱን የነበረ ሲሆን ድሬዎች በበኩላቸዉ በተሻጋሪ ኳሶች ወደ አዳማ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት እያደረጉ ተደጋጋሚ ሙከራዎች በሁለቱም በኩል እየተደረገ ጨዋታዉ 1-1 በሆነ ዉጤት እስከ 82ኛ ደቂቃ ድረስ ማምራት ቢችልም ዮሴፍ ታረቀች ለአዳማ ከተማዎች መሪ መሆን የቻሉበትን ጎል አስቆጥሮ አዳማ ከነማዎች ከዋላ ተነስተዉ 2-1 በሆነ ዉጤት መሪ መሆን ችለዋል።
የድሬዎቹ ግብ ጠባቂ ዳንኤል ጉዳት አስተናግዶ በፍሬው ተቀይሮ ከሜዳ የወጣ ሲሆን እንዲሁም በጨዋታዉ መገባደጃ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የአዳማ ከተማዉ አድናን ረሻድ ከዳኛ ጋር ሰጣ ገባ ዉስጥ በመግባቱ በሁለት ተከታታይ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ከተሰናበተ በኋላ የእለቱ ጨዋታ በአዳማ ከተማ አሸናፊነት 2-1 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።