በሁለተኛ ዙር ጠንክሮ ለመምጣት እየሰሩ ያሉት ወላይታ ድቻዎች ለቀጣዮቹ 6ወራት ጋቶች ፓኖምን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ሁለቱ ወገኖች በደመወዝና ጥቅማጥቅሞች የተስማሙ ሲሆን ተጨዋቹ ዛሬ ልምምዱን ለመጀመር ወደ ወላይታ አቅንቷል።
ወላይታ ድቻ በቀጣይ በ11ኛው ሳምንት መርሃግብር የካቲት 12 ባህር ዳር ከተማ ላይ ሲቀጥል ከባህር ዳር ከተማ ጋር የሚጫወት ይሆናል። የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወላይታ ድቻ በ10 ነጥብና 3 የግብ እዳ በሊጉ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።