ሰሞኑን የነባር ተጫዋቾቻቸዉን ዉል በማደስ ላይ ተጠምደዉ የነበሩት አፄዎቹ በትላንትናው ዕለት የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን መናፍ አወልን የመጀመሪያ ፈራሚ በማድረግ ወደ ስብስባቸዉ መቀላቀላቸዉ ይታወሳል።
በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ሁለተኛ ፈራሚ በማድረግ የመስመር አጥቂዉን ሀብታሙ ገዛኸኝን ወ። ስብስባቸዉ መቀላቀላቸው ተረጋግጧል ።
ከዚህ ቀደም ለደቡብ ፖሊስ መጫወት የቻለዉ እና ያለፉትን አራት አመታት ያህል በሲዳማ ቡና ቤት ማሳለፍ የቻለዉ ተጫዋቹ ለሁለት አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል አፄዎቹን መቀላቀሉ ይፋ ተደረጓል።