By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Reading: ወልቂጤ ከተማና አዳማ ከተማ በደመወዝ ጠያቂ ተጨዋቾች ተወጥረዋል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ሾለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
Š 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችአዳማ ከተማወልቂጤ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ወልቂጤ ከተማና አዳማ ከተማ በደመወዝ ጠያቂ ተጨዋቾች ተወጥረዋል

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

👉 አመራሮቹ ዝምታን መርጠዋል…

ወልቂጤ ከተማ ደመወዝ ከከፈለን አምስት ወር አልፎናል ከዚህ በኋላ አንታገስም ያሉ በርካታ ተጨዋቾች ከሆቴል መውጣታቸው ታውቋል።

ክለቡ ኢትዮጵያ ቡናን ከመግጠሙ በፊት የወልቂጤ ከተማ አመራሮች ተጨዋቾችን አነጋግረው በ3 ቀን ውስጥ ደመወዝ እንደሚከፍሉ ቃል ገብተው ቢሄዱም አሁን ድረስ ምላሽ እንዳልተሰጣቸውና ስልክ ሲደወል እንደማያነሱ ተጨዋቾቹ ይናገራሉ። ትዳራቸውን መምራት ያቃታቸው ጫና ውስጥ ያሉ ሃላፊነታቸውን መወጣት ያልቻሉ ተጨዋቾች መኖራቸው ትልቅ ሀዘን ውስጥ እንደከተታቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ተጨዋቾች እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

“ለክለቡ፣ ለማህበረሰቡና ለደጋፊው ትልቅ ክብር አለን” ያሉት ተጨዋቾቹ “ለጥቅምት 15 የተሰጠን ቼክ አሁን ድረስ ሳይከፈለን ሶስት ወር ሞላን ለባንኮች ሄደን ያልከሰስነውና ያላስመታነው ለዚህ ነው አሁን ግን በዝቷል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ጥረት ተጫውተናል ከአሁን በኋላ ግን ከብዶናል በማለት ለፌዴሬሽን ማመልከታቸውና ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊያየው መሆኑም ተሰምቷል። ከቡድኑ አባላት መሃል ወደ 16 የሚጠጉ ቡድኑ ካረፈበት ሆቴል የወጡ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የፊታችን እሁድ 9 ሰአት ከሀዋሳ ከተማ ጋር የሚያደርጉት 13ኛ ሳምንት ጨዋታ የመደረጉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

- ማሰታውቂያ -

በዚህ ጉዳይ ያለውን የክለቡን ምላሽ ለማወቅ የቡድን መሪ ወደ ሆኑት አቶ አዲስ ወልዴ የደወልን ሲሆን ስልኩን አንስተው ጥያቄያችንን ከሰሙ በኋላ ይቆራረጣል አይሰማም በማለት ከመዝጋታቸውም በተጨማሪ በተደጋጋሚ ጊዜ ብንደውልም ቴክስት ብንልክም ባለመመለሳቸው የክለቡን ምላሽ ማወቅ አለመቻላችንን እንገልጻለን። ወልቂጤ ከተማ በእስካሁኑ 12 ጨዋታዎች 9 ነጥብና 11 የግብ ዕዳ ይዞ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል…

በተመሳሳይ አዳማ ከተማም በጨዋታ ሂደት በተለምዶ ከቋሚ 11 ውስጥ ናቸው ከሚባሉት ተጨዋቾች መሃል አምስቱ ቡድኑ ካረፈበት ሆቴል ወጥተዋል። አምስቱም ተጨዋቾች እንደሌሎቹ ተጨዋቾች የሶስት ወር ደመወዝና የፊርማ ክፍያ ያልተከፈላቸው በመሆኑ ቅሬታቸውን ለመግለጽ ቡድኑን ተነጥለው ወጥተዋል።

የቡድኑ አመራሮች ዘንድሮ ከአምስት ጊዜ በላይ መጥተው በሶሰት አራት ቀን ውስጥ ይከፈላል በማለት ቃል ቢገቡም ተፈጻሚ ሳያደርጉ ቀርተዋል። “ወደ 12 ጨዋታ ታግሰን ቆይተናል እስካሁንም መረጃው እንዳይወጣ የምንችለውን አድርገናል አሁን ግን ቤተሰባችንን የልጆቻችንን የትምህርት መክፈል እስካለመቻል በመቸገራችን ለምንወስደው ርምጃ ሃላፊነቱ የአመራርቹ ነው” በማለት አስጠንቅቀዋል። አዳማ ከተማ በፕሪሚየር ሊጉ 13ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዳሜ 12 ሰዓት ከባህር ዳር ከተማ ጋር የሚጫወት ሲሆን በ18 ነጥብና 2 ግብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የበርካታ ደጋፊ ባለቤት የሆነውና በሊጉ ታሪክ ጥንካሬያቸው ከሚወሳላቸው ክለቦች መሃል አንዱ የሆነው አዳማ ከተማ ከውጤት ይልቅ ደመወዝ ለመክፈል ከሚቸገሩት የሊጉ ክለቦች መሃል አንዱ መሆኑ እስከመቼ ይቀጥላል የሚለው የበርካታ ደጋፊዎቹ ጥያቄ ሆኗል።

በዚሁ የተጨዋቾቹ ቅሬታ ዙሪያ የክለቡን ምላሽ ለማወቅ ወደ ፕሬዝዳንቱ አቶ አንበሴ መገርሳ የእጅ ስልክ ብንደውልም ባለመመለሳቸው የክለቡን አቋም ማወቅ አልቻልንም።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article “በሀምበሪቾ ደስተኛ ነኝ ግን ደመወዝ የለም ጥቅማ ጥቅምም የለም ቤተሰቤን መምራት ከበደኝ” ቴዎድሮስ በቀለ /ሀምበሪቾ ዱራሜ/
Next Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችፋሲል ከነማ

ፋሲል ከነማ ይግባኝ ሊጠይቅ ነው

ቴዎድሮስ ታከለ By ቴዎድሮስ ታከለ 2 months ago
የሴቶች የዝውውር ዜና
ኪቲካ ጀማ አዲሱ የነገሌ አርሲ ተጫዋች ሆኗል
La liste des 24 joueurs qui oppose le Niger dĂŠvoilĂŠe
ለተከበራችሁት የሀትሪክ ቤተሰቦች ዛሬ ለንባብ በወጣችው ሀትሪክ ጋዜጣ ላይ ከአስቻለው ታመነ ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስ ቅሬታ መፍጠሩን ተረድተናል።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

Š Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?