ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 2ኛ ሳምንት በተደረጉ ሰባት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ 21 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ማጣሪያ ምክንያት በሳምንቱ ያልተካሄደው ብቸኛው የወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ በተስተካካይ ሕዳር 27 በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ይታወቃል። በሳምንቱ 30 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ የተገሰፁ ናቸው።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 1/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በክለቦች ደረጃ ሃዋሳ ከተማ ባደረገው የ2ኛ ሳምንት ጨዋታ የቡድኑ 6 ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ኢትዮ ኤሌትሪክ ባደረገው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል እንዲሁም ለክለቡ የቡድን መሪና የደጋፊ ማህበር ተወካይ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴው ለማነጋገር ጥሪ አድርጓል፡፡
- ማሰታውቂያ -
©Eplsc