የ2015 አመት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጦች ዛሬ ምሽት በሀያት ሪጀንሲ በርካታ የስፖርቱ እና እግርኳሱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተገኙበት የእውቅናና የሽልማት መርሐግብር ተከናውኗል።
በዚህም መሰረት የአዳማ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ዮሴፍ ታረቀኝ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ2015 ዓመት የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ መድኑ ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ2015 ዓመት የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመባል ሲመረጥ ፤ የቀድሞዉ የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጫዋች ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ ደግሞ በ25 ጎሎች የውድድር አመቱ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመባል ሽልማቱን በተወካዩ አማካኝነት ተቀብሏል።
- ማሰታውቂያ -
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ2015 የአመት የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ሲመረጥ ፤ አመቱ ምርጥ ዳኛ በመባል ቢኒያም ወርቅአገኘሁ ሲመረጡ ምርጥ ረዳት በመሆን ደግሞ ትግል ግዛው መመረጥ ችሏል ።
በመጨረሻም የቅዱስ ጊዮርጊሱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ቢኒያም በላይ የውድድር አመቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ምርጥ ተጫዋች በመባል መመረጥ ሲችል ፤ 210 ሺህ ብር እና የዋንጫ ሽልማትም ከአዘጋጆቹ ተሸልሟል ።