በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመሩ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት እና የ2016 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆን የቻሉት ሻሸመኔ ከተማዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት እለት ታዉቋል።
ለ2016 ዓ.ም ለዉድድር ዘመን አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ እየቀላቀሉ እንዲሁም የነባር ተጫዋቾችን ዉል በማደስ ላይ የሚገኙት ሻሸመኔ ከተማዎች ቅድመ ዝግጅታቸዉን በቢሾፍቱ ከተማ በኳሊቲ ሆቴል በማረፍ ከሰኞ ከነሀሴ 15 ጀምሮ እንደሚያደርጉ ለማወቅ ችለናል።
ሻሸመኔ ከተማዎች አሁን ያላቸዉ ስብስብ ላይ በቅርቡ አዳዲስ የሀገር ዉስጥ እና የዉጪ ሀገር ተጫዋቾችን እንደሚጨምሩ ለማወቅ ችለናል።