By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ፌዴራል አርቢትር  ቢኒያም ወርቅአገኘሁ የአመቱ ኮከብ አርቢትር….?
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

ፌዴራል አርቢትር  ቢኒያም ወርቅአገኘሁ የአመቱ ኮከብ አርቢትር….?

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 3 years ago
Share
SHARE

*…. በ9 አመት ውስጥ የተገኘና  የኢንተርናሽናል
አርቢትሮች ግዛትን የጣሰ አርቢትር ሆኗል……

*…. ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛውም ለሁለት
አመታት በተከታታይ ያሸነፈ ረዳት አርቢትር ሆኗል…

*…  ከአመታት በፊት የነበረው የኮከብ ዳኞች 25 ሺህ
ብር ሽልማት ወደ 110 ሺህ ብር ማደጉ ምርጫውን
ተጠባቂ አድርጎታል…

የ2015 የአመቱ የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከቦች የሽልማትና  የሊጉ የመዝጊያ ስነስርዓት  ዛሬ ምሽት በሀያት ሪጀንሲ  በሚካሄደው መርሃግብር ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

- ማሰታውቂያ -

በእስካሁኑ  ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ሁለተኛው ባህርዳር ከተማ ሶስተኛው ኢትዮጵያ መድን  መሆናቸው የኮከብ ግብ አግቢነቱን የፈረሰኞቹ እስማኤል ኦሮ አጎሮ በ25 ግብ  ከማሸነፉ  ውጪ  በርካቶቹ አሸናፊዎች ዛሬ ምሽት የሚታወቁ በመሆኑ ማነው ኮከብ የሚለው ትኩረት አግኝቷል።

የሽልማት ስነስርዓቱ ሊጀመርና  ኮከቦቹ ሊለዩ ሰዓታት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት ከታማኝ የመረጃ ምንጭ በተገኘ መረጃ ቢያንስ ባለፉት ስምንት  አመታት ኢንተርናሽናሎች ብቻ የደመቁበትን መድረክ  ፌዴራል አርቢትር ቢኒያም
ወ/አገኘሁ መጋራቱ የተረጋገጠ ሆኗል። የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሙሉ መረጃውን ዛሬ  ከቀትር በኋላ ይፋ እንደሚያድርገው  ይጠበቃል።

በአመቱ የኮከቦች ምርጫ  በተለያዩ መመዘኛዎች የተሻለ ነጥብ አግኝተዋል የተባሉት ኢንተርናሽናል ረዳት አርቢትር ትግል ግዛው የአመቱ ምስጉን  ረዳት ዳኛ ዘርፍ በተከታታይ ለሁለኛ ጊዜ ማሸነፉ ታውቋል። ይህም ከረጅም አመታት በኋላ የተገኘ ትልቅ ክስተትም ሆኗል። የዋና ዳኝነቱን የኮከብነት ቦታ ፌዴራል አርቢትር ቢኒያም ወ/አገኘሁ ባለፉት ሁለት አመታት በተከታታይ ያሸነፉትን ኢንተርናሽናል አርቢትሮች በላይ ታደሰና ሃይለየሱስ ባዘዘውን አስከትሎ ከአመታት በኋላ ለፌዴራሎች ተስፋ ሰጪ የሆነ አሸናፊ ሆኗል።

በተለይ ኢንተርናሽናሎች ብቻ ለምን ይመረጣሉ ?  በብቃት ከሆነ ፌዴራል አርቢትሮችም እድሉን ማግኘት አለባቸው በማለት በማህበርም በግልም ሲታገሉ ለነበሩት ዳኞች እንደ ትልቅ ስኬት ተቆጥሯል። ፌዴራል ዳኛ ሆኖ ኮከብ ከተባለ ኢንተርናሽናል ዳኛስ ለምን አልተደረገም ተብለን ጫና ውስጥ እንገባለን ለዚህም ኮከብነቱን አንሰጥም ሲሉ ለነበሩ ኮሚቴዎች በኮሚሽነር ሸረፋ ደሌቾ የሚመራው ኮሚቴ  የሰጠው ውሳኔ አይን ገላጭ ውሳኔ ነው ተብሏል።

በአምናው የሽልማት መድረክ ላይ ከነበሩት ተሸላሚዎች ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ትግል ግዛውና ሻምፒዮኑ የቅ/ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ዳግም በዛሬው የሽልማት መድረክ ላይ የሚታዩ ይሆናል ተብሎ ይገመታል። በኮከቦቹ አርቢትሮች ምርጫ ላይ ምናልባት የሚነሳ ቅሬታ  ሳይኖር እንደማይቀር የገመተው ምንጫችን ኮሚቴው  የተአማኒነት ክስ እንዲነሳበት የሚያደርግ ውሳኔ ወስኖ ይሆን ? የሚል ጥያቄንም አቅርቧል።

በአቶ  ጁነዲን ባሻ እና በአቶ ኢሳያስ ጅራ አራት አራት አመት የፕሬዝዳንትነት ዘመን በስምንት አመት ውስጥ ያልተሞከረውንና ዘንድሮ  የተደፈረው የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ውሳኔ ምን ቅሬታና ደስታ ይፈጥር ይሆን ? የዳኞቹስ ምላሽስ..? የሚለው በቀጣዮቹ ቀናቶች የሚታወቅ ይሆናል። በአቶ ኢሳያስ ሁለተኛ የስልጣን ዘመን የመጀመሪያ አመት ያልተደፈረው ተደፍሯል ተብሏል።

ከ25 ሺህ ብር ያልበለጠ  የኮከብነት ሽልማት ይሰጥ በነበረው የሽልማት ስነስርአት  ባለፉት ሁለት አመታት ግን  የኮከብ ዳኞቹ  ሽልማት በከፍተኛ ሁኔታ ያደገ ሲሆን  ያለፉት ሁለት አመታት  ተሸላሚዎች እያንዳንዳቸው 110 ሺህ ብር መሸለማቸው ይታወሳል…ዘንድሮስ..? የሚለው ዛሬ ምሽት የሀያት ሪጀንሲ ሆቴል የመዝጊያ መርሃግብር ላይ የሚታወቅ ይሆናል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article 0አፄዎቹ የፊት መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል !!
Next Article ሻሸመኔ ከተማዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት እለት ታዉቋል።

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
Uncategorized

ሀገር አቀፍ የክልል ሻምፒዮና ወደ አንደኛ ሊግ ያለፉ አራት ክለቦች ታውቀዋል

Mussie Girmay By Mussie Girmay 9 years ago
ሰበታ ከተማ ጦሮቹን በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል
ለኢትዮጵያዊው የቀድሞ ተጨዋች ሀብቶም ብርሃኔ ለቀረበለት የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሹን ከስዊዘርላንድ ሰጥቷል
ፊፋ 21 ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞችን ይፋ አደረገ የኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ኮታ ዝቅ ማለቱ ቅሬታ ፈጥሯል
ሲዳማ ቡና የወሳኝ ተጫዋቹን ዉል ሲያራዝም እንዲሁም የግራ መስመር ተከላካይ አስፈርሟል።
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?