19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የፍፃሜ ውድድር ከደቂቃዎች በፊት ሲጠናቀቅ የወርቅ ፤ የብር እና የነሐስ ሜዳልያዎቹን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ወስደዋል ።
በርቀቱ የኦሪገኑ 18ኛው የአለም ሻምፒዮና የ5 ሺህ ሜትር አሸናፊ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በ31:27.18 በአንደኝነት አጠናቃለች ።
ጉዳፍ በመጨረሻ ሜትሮች ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር ከባድ ፉክክር አድርጋለች ።
አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ31:28.16 2ኛ እንዲሁም አትሌት እጅጋየሁ ታዬ በ32:28.31 የ3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ፈፅመዋል ።