መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 8ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ

አጋራ
አጋራ

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 87ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አምስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሶስት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ 23 ጎሎች በ22 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አምስት በፍፁም ቅጣት ምት አንድ በራስ ላይ ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 35 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 11/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በተጫዋች መክብብ ደገፉ(ሲዳማ ቡና) ክለቡ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ባደረገው ጨዋታ የተጋጣሚን ቡድን ግልፅ ግብ ዕድል በማበላሸት ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በክለቦች አርባምንጭ ከተማ እና ፋሲል ከነማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለባቸው አምስት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...

መቐለ 70 እንደርታዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ዘርአይ ሙሉ በቴክኒክ አማካሪነት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ተመልሷል

አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል። በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ...