መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከቡድኑ ጋር ይቆያል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ከቡድኑ ጋር ይቆያል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮ ኤሌክትሪክ ቦርድ ከአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና ጋር ከተወያየ በኋላ ወደ ድሬዳዋ እንዲመለስና ከቡድኑ ጋር እንዲቆይ ወሰነ።

ትላንት አዲስ አበባ ገብቶ ዛሬ ከቦርዱ ጋር የተገናኘው አሰልጣኙ ቡድኑ ጋር ያለውን ጠንካራና ደካሜ ጎን ያስረዳ ሲሆን ቦርዱ ራሱ ውስጡን እንዲመረምር አንድ የደጋፊ ማህበሩ አመራርና አንድ የቦርድ አባል ቡድኑ ላይ የፈጠሩትን ችግርና ጫና በማስረዳት ያለውን እውነት ገልጿል

ቦርዱም በሰጠው ውሳኔ በአሰልጣኝ ክፍፍሌ የማይፈለገውን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ መሃመድን ወደ ከ20 አመት በታች ቡድኑ እንዲመለስ፣ የቡድን መሪው አቶ በድሉ እና የህክምና ባለሙያዋ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ አዟል።

አሰልጣኙ በቀጣይ ቡድኑን ወደ ውጤት እንዲመራ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ተነግሮት ወደ ድሬዳዋ እንዲመለስ በመወሰኑ በሶሰት አሰልጣኞች የተደረገው ስርሰራ መክሸፉ ታውቋል። ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ8ኛው ሳምንት መርሃግብር ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ግጥሚያውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...