By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የአዲሰ አበባ ስታዲየም ተካሄደ በተባለው ዝርፊያ ተጠርጥረው በፖሊስ የተያዙት ተጠርጣሪዎች በሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምክንያት እንዲፈቱ መደረጉ ቁጣ ቀስቅሷል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንዜናዎች

የአዲሰ አበባ ስታዲየም ተካሄደ በተባለው ዝርፊያ ተጠርጥረው በፖሊስ የተያዙት ተጠርጣሪዎች በሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ምክንያት እንዲፈቱ መደረጉ ቁጣ ቀስቅሷል

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

*….ስታዲየሙ ያሉት ንብረቶች የኔ ነው በሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ፌዴሬሽኑ እየተወዛገቡ ነው…

*…ቀድሞ የነበሩት የስታዲየሙ ወንበሮች የት እንደደረሱ አልታወቀም….

*….. ኪሎውን ተመዝኖ የመጣው ሲኖትራክ ትሪቩን ውስጥ እንዳለ ተይዟል….

በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጀት ተይዞለት ዕድሳት ላይ ያለው የአዲሰ አበባ ስታዲየም የውስጥ ብረቶችን በሲኖትራክ መኪና እየጫነ የነበረው ሹፌር ከነ መኪናው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

- ማሰታውቂያ -

እድሳቱ የዘገየውና እየተጓተተ የመጣው የአዲስ አበባ ስታዲየም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ ያላቸው ንብረቶች በሙሉ ሲጓዙ መቆየታቸው የአደባባይ ሚስጢር እንደነበር የሚናገሩ በርክተዋል። ከትላንት በስቲያ ምሽት አንድ ሲኖትራክ መኪና ስታዲየም ውስጥ በመግባት ከፍተኛ ወጪ ያላቸውን ብረቶች መኪና ውስጥ እየጫነ እያለ የፌዴሬሽን ሰዎች ደርሰውበት ለፖሊስ በተሰጠው ጥቆማ ሹፌሩ የተያዘ ሲሆን መኪናዬ ተመዝኖ የምወስደውን ብረት ጭኜ እንድወጣ ታዝዤ የመጣሁት የሚል ምላሽ ቢሰጥም ከነመኪናው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ እዚያው ማደሩ ታውቋል። በዚህ ዝርፊያ ላይ የተጠረጠሩት ግለሰቦችና የባህል ስፖርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ትላንት ተይዘው የነበረ ቢሆንም ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ያዘዝኩት እኔ ነኝ በማለታቸው ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ እንዲለቀቁ መደረጉ ቅሬታ ፈጥሯል።

ሚኒስቴር ደኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት እሳቸውና ሚኒስትሩ በቦታው ላይ ሳይመጡ ጭምር ብዙ ንብረቶች በመጥፋታቸው ይሄን ብቻ ሳይሆን ከበፊቱ ጀምሮ የነበረው ምዝበራ እንዲጣራ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህግ ክፍል ደብዳቤ መጻፋቸው ታውቋል። እጅ ከፍንጅ ተያዘ የተባለው ግለስብ ላይ ምርመራው ተጠናክሮ ባለበት ሂደት የስታዲየሙ ጥበቃዎች ቃል ሰጥተው በተመለሱበት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ “አካባቢውን አጥሩና ለምርቃት አዘጋጁ ብዬ ያዘዝኩት እኔ ነኝ” በማለታቸው የተያዙት ሰራተኞች መለቀቃቸው በሁለቱ አመራሮች መሃል ልዩነት መፈጠሩን ያሳየ ሆኗል።

“አቶ ቀጀላ ያዘዙት ምንድነው..? ቆሻሻዎቹ እንዲጠረጉና አካባቢው ንጹህ እንዲሆን ወይስ ንብረቶቹ እንዲዘረፉ ” የሚሉት ወገኖች ስታዲየሙ ቀድሞ የነበረው ወንበር ብረቶችና የተለያዩ ንብረቶች የት እንዳሉ ሚኒስትሩና ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ምላሽ እንዲሰጡበት ይጠይቃሉ። በአዲስ አበባ ስታዲየምና በአደይ አበባ ስታዲየም የነበሩትን ብረቶችና ንብረቶች የት እንዳሉ የማይታወቅ ሲሆን ምናልባት ለመመዝበሩም ግንባታውን የሚመራው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ አመራሮቹና በቀጥታ የሚመለከታቸው ሃላፊዎች መጠየቅ እንዳለባቸው ተጠይቋል።

የአዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ ያሉት ንብረቶች የኔ እንጂ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አይደለም የሚለው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ከዚህ በፊት የስታዲየሙ ወንበሮች ሲገጠሙ ጨረታውን ያወጣው ፌዴሬሽኑ በመሆኑ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ የኔ ነው የሚልበት ምክንያት የለውም በማለት ንብረቶቹ በመመዝበራቸው ማጣራት ተደርጎ ጥፋተኞቹ ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ለፖሊስ በደብዳቤ መጠየቁ ታውቋል።

ባለፉት አመታት ከእደሳ ጋር ተያይዞ የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ ብረቶች ወንበሮችና ልዩ ልዩ ንብረቶች ሲወጡ እንደነበር የቅርብ ምንጮች ይናገራሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውሴጥ ያሉ ሰንሰለቶች ካልተበጠሱ የቆየው የንብረት ማሸሽና ዝርፊያ ሊቀጥል ይችላል ተብሎም ተሰግቷል። እስካሁን የተነቀሉት የሙሉ ስታዲየም ወንበሮች ብረቶችና ንብረቶች የት እንደገቡ የማይታወቅ በመሆኑ ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ የት እንዳሉ የማብራራት ግዴታ እንዳለባቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የይገባኛሉ ክርክር አሸናፊ ማን እንደሆነ ባይታወቅም የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ላይ እንዲገኙ ካፍ ለአፍሪካ ሀገራት እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች ባቀረበው ጥሪ መሰረት ወደ አቢጃን ያቀኑት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከኮትዲቯር ሲመለሱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርች ጋር በሚያደርጉት ውይይት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

You Might Also Like

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
Next Article የዕለቱ ሁለት ተጠባቂ መርሐግብሮች በተመሳሳይ በአቻ ዉጤት ፍፃሜያቸዉን አግኝተዋል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሪፖርትየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎች

​ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳው ውጪ የመጀመሪያ ድሉን ድሬ ላይ አስመዝግቧል፡፡

hatricksport team By hatricksport team 8 years ago
አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ከባህርዳር ከተማ ጋር ለመቆየት ተስማምቷል
የጨዋታ ዘገባ | ቡናማዎቹ ወደ አሸናፊነት ተመልሰዋል !!
ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ | የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ
ሲዳማ ቡና የተከላካዩን ኮንትራት አራዝሟል!
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?