በእግርኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የባህርዳር ከተማ ሊካሄድ 36 ሰዓት በቀረበት ወቅት የባህርዳር ደጋፊዎች ላይ የደረሰው የቦንብ ጥቃት አነጋጋሪ ሆኗል።
ደጋፊዎቹ ቡድናቸውን ለመደገፍ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተፈቀደላቸውን አውቶቢስና ሌላ በተከራዩት ተጨማሪ አውቶቢስ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ለሊት 10
ሰዓት ላይ በሙላለም የባህል ማዕከል አየተሰባሰቡ ባሉበት አደጋው መድረሱ ታውቋል በጉዳቱ እስካሁን የሞተ ሰው የሌለ ሲሆን ከ20 የሚበልጡ ደጋፊዎች ግን
ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል።
ቦንቡ ተወርውሮ ይሁን ተጠምዶ በሚለውና አጠቃላይ ጉዳት ዙሪያ የክልሉ መንግስትና ፖሊስ የሚሰጠው መግለጫ ይጠበቃል።