ፈረንሳይ ፓሪስ በሚካሄደው የኦልምፒክ ውድድር 200ሺህ ዲያስፖራ በፓሪስ እንዲገኝ ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሎመምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ተናገሩ።
ዛሬ ከቀትር በኋላ በማሪዮት ሆቴል በተሰጠ መግለጫ የፓሪስ ኦሎምፒክ የብሄራዊ ዝግጅት ኮሚቴ ዝግጅትን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር አሸብር እንደተናገሩት
በአምሰተርዳም በተካሄደ የ2 ቀን ውድድር 30ሺህ ዲያስፖራ መገኘቱን በማየት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ጋር ተገኝተን ከነበሩት የዲያስፖራ አባላት ጋር ያደረግነውን ምክክር ታሳቢ አድርገን ጠንክረን እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በፓሪስ ኦሎምፒክ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አሸብር ለስኬቱ የንግዱ ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብየቷል ክቡር ጠ/ሚ ዶክተር አቢይ አህመድ አትሌቶችን እየመሩ እንዲጎዙ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው የሚነስቴር መስሪያ ቤቴቶች የሚዲያ ተቋማት የክልል መንግስታት በጋራ ከቡድኑ ጋር ለማስኬድ ከቡድኑ ጎን እንዲሆኑም ጥሪ አቀርባለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
” የአትሌት ምልመላና ምርጫ ላይ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አንድም ተሳትፎ የለውም ይሄ መታወቅ አለበት ያሉት ዶክተር አሸብር ቀነኒሳ በቀለን ወደ ውድድሩ እንዲመለስ ታግለን ጥረት አርገን ተሳክቶልናል አንድም አትሌት ለመጉዳት ብለን ያደረግነው ነገር የለም ያልተመረጡ አትሌቶች አንሰው የተመረጡ ደግሞ በጣም በልጠው አለመሆኑን ማዘወቅ አለባቸው ነገ የአለም ሻምፒዮን አለ ለዚያ ብንዘጋጅ ጥሩ ይመስለናል ሲሉም መልሰዋል።
- ማሰታውቂያ -
ከረዳት ኮሚሽነርጰ ደራርቱ ቱሉ ጋር ተፈጥሮ ስለነበረው ልዩነት ለቀረበው ጥያቄ ዶክተር አሸብር በሰጡት ምላሽ ፌዴሬሽኑና ስራ አስፈጻሚው የኦሎምፒክ ኮሚቴና ቦርዱ ረስተን እየሰራን አመት ያለፈውን ክስተት አሁን መጠየቅ ለምን አስፈለገ..? በጋራ ለአንድ አላማ እየተጋን እያለ ለምን ይህን እናስባለን ችግር እንዲፈጠር ለምንስ እንጣውልጋለን ለአንድ አላማ እየተጋን ነው በውስጣችሁ መጥፎ ሃሳብ ካለ ከውስጣችሁ አውጡት በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።
“አሰልጣኞችን በተመለከተ ጥሩ ክፍያ የለም
መንግስት የክልል ተቋማት እንዲያግዙን እየሰራን ነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቦርድ በጋራ እየሰራን ችግር ሲከሰት እያረምን እየሰራን ስለሆነ ከእግዛዚአብር ርዳታ ጋር ውጤታማ የምንሆን ይመስለኛል” ያሉት ዶክተር አሸብር አሰልጣኝ እንደ አትሌቱ ለምን አይከፈለውም የሚለው ጥያቄ ትክክል ነው ነገር ግን የችግሩ ምንጭ ለበላይ አካል ጥናት የሚያቀርቡት ባለሙያዎች ልዩነት መፍጠራቸው ያመጡት ጣጣ ነው ይሄ መስተካከል አለበት የቀድሞ ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በነበሩበት ጊዜ ወርቅ ላመጣ አትሌትና ለአሰልጣኙ እኩል ይከፈል ተብሎ ጥናቱን አጣመው ያስቀሩት ባለሙያዎች ናቸው
በእኛ እምነት ወርቅ ያመጣ አትሌትም ሆነ አሰልጣኙ እኩል ሊሸለሙ ይገባል መንግስት ሙሉ ድጋፍ ያደረጋል በናንተ በኩል ተግታችሁ በርትታችሁ ስሩ በዚህ በኩል ክፍተት ይመጣል ብላችሁ አትስጉ ሲሉ አሰልጣኞቹን መክረዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ” ከሚያዚያ 28/2016 ጀምሮ ወደ 60 የሚጠጉ አትሌቶቹ ሆቴል ገብተው ልምምዳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል አብይ ኮሚቴውም በሚገባ እየተከታተለ ነው ከዚያ ውጪ በ10 ሺህ ሜትር ወንድና ሴት በ1500 እና በ800 ወንድ አትሌቶች ሚኒማ እንዲያሟሉ በስፔን ማላጋ ውድድር ተዘጋጅቷል ስትል ተናግራለች።
በርግጥም የማዘውተሪያ ችግር አለ ችግሩ የሀገር ችግር እንደመሆኑ ተቻችለን ማለፍ ይጠበቅብናል ከዚያም ውጪ ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ ለስልጠና የሚሆን ቦታ ብናገኝም አትሌቶችና አሰልጣኞች ከውድድሩ አየር የተነሳ እዚሁ እንሰልጥን በማለታቸው ቀርቷል’ ያለችው ረዳት ኮሚሽነሯ እውነት ነው ያለበቂ ክፍያ የሚሰሩ አሰልጣኞች አሉን እነሱ ኢትዮጵያ ሀገራቸውን አስቀድመው ክብር ለኢትዮጵያ ባንዲራ በሚል እየሰሩ በመሆናቸው እናመሰግናለን እንደ ጥሩ ዝግጅታችን ከእግዜር ጋር ውጤት ለማምጣት እንጥራለን ስትልም ተናግራለች። ስለ አሰልጣኝ ምርጫ የተገረችው ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ አትሌቶች በሚኒማ ሲመረጡ አሰልጣኞች ደግሞ ባስመረጡት አትሌት ብዛት ይመረጣሉ በማለት ምላሿን ሰጥታለች።
በዕለቱ የተገኘው አሰልጣኝ ረዳት ኮሚሽነር ሁሴን ሼቦ
ለኦሎምፒኩ ድል በሚመጥን ደረጃ ጠንክረን እየሰራን ነው እስካሁን ግን ምላሽ ያጣነው የሜዳ ችግር ነው በሜዳ ችግር ምክንያት በ 800 እና በ1500 ሚኒማ ያሟላ አትሌት የለንም”” ሲል ተናግሯል። የጀግኖች አትሌቶች አሰልጣኝ የውጪ አሰልጣኝ ቢሆን የሚያገኘው እውቅና ታላቅ እንደሚሆን እናውቃለን እኛ ሀገር ግን እውቅና አልተሰጠንም ያም ሆኖ ለሀገር ክብር ለህዝቧ ደስታ በእልህ በቁጭት እየሰራን ነው ውጤታማ ሆነን እንደምንመጣ ተስፋ እናደርጋለን” ሲል ተናግሯል።
በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጋራ ለፓሪሱ ኦሎምፒክ ስኬት ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን በመግለጽ መላው ህብረተሰብ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አድርገዋል።