የቀድሞው የሲዳማ ቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስ የአሁኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨዋች የሆነው አዲስ ግደይ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግብ አስቆጥሮ ያሳየው ምልክት መነጋገሪያ ሆኗል… ተጨዋቹ የክለባችንን ምልክት ነው የዘቀዘቀው በማለት የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ሲቃወሙት ታይቷል ….በተገኘው ምክንያት መበሻሸቅ ልማዳቸው የሆነው የኢትዮጵያ ቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሲነቋቆሩ ቢሰነብቱም ተጨዋቹ ግን ከሀትሪክ ድረገጹ ባልደረባ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበረው ቆይታ ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሏል….
ሀትሪክ:- አዲስ አመሰግናለሁ..ላሳየኧን ፈቃደኝነት..
አዲስ:- እኔም በጣም አመሰግናለሁ
ሀትሪክ :- እስቲ ስለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሰላፊነትህ እናውራ…?
- ማሰታውቂያ -
አዲስ :- በታሪኬ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የተቀላቀልኩት …ክለቡም አዲስ አዳጊ ቡድን ነው አራት የሊግ ጨዋታዎችን አድርጌያለሁ ጥሩ የሚባል አጀማመር አድርገናል… አዲስ አዳጊ ይሁን እንጂ ሲኒየር ተጨዋቾችን ማካተቱ አጀማመሩን ጥሩ አድርጎታል በቀጣይም የተሻለ አቋም ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ …አጀማመራችን ግን አሪፍ ነው….
ሀትሪክ:- ቅዱስ ጊዮርጊስን በጉዳት ለቀቀክ ..? ወይስ ..?
አዲስ:- በፍጹም …ይሄ በግልጽ መታወቅ አለበት በርግጥ ከሁለት አመት በፊት ጉዳት አጋጥሞኝ ነበር ከዚያ በኋላ በጥሩ ሁኔታ አገግሜ በጥሩ አካል ብቃትና ስነልቦና ወደ ውድድር ተመልሼ ጥሩ ልምምድ ስሰራ ቆይቻለሁ…በ2015 ግን በተለይ ከጥቅምት ጀምሮ በጥሩ ዝግጅት አሰልጣኞቼ የሚሰጡኝን ስልጠና በብቃት ስወጣ ቆይቼ ለጨዋታ ዝግጁ ብሆንም ግጥሚያ ማድረግ አልቻልኩም …. ብዙ የመሰለፍ እድል አላገኘሁም ለጨዋታው ግን ዝግጁ ነበርኩ የኔ ሃላፊነት ዝግጁ መሆን ነበር ዝግጁም ሆኜ አሰልጣኜ የሚለኝን ስሰራ ቆይቻለሁ የአሰልጣኙ ምርጫና ውሳኔ ሆኖ ብዙ ጨዋታ አልተሰለፍኩም እንጂ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ እንደነበርኩ መታወቅ አለዘት..
ሀትሪክ:- ስለዚህ ንግድ ባንክ ጤነኛውና ባለልምዱን አዲስ ግደይን ነው ያገኘው ማለት ይቻላላ…?
አዲስ:- አዎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገባሁት በሙሉ ጤነኛ ሆኜ ራሴን ለማሳየት ለጨዋታው ዝግጁ ሆኜ ነው..
ሀትሪክ:- ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ምን ለማሳካት አቀድክ..?
አዲስ:- ዘንድሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የተቀላቀልኩት የቀድሞውን አዲስ ግደይን የመመለስ እቅድ ይዤ ነው .. አጀማመራችን ጥሩ ነው ከፍተኛ የሆነ በራስ መተማመን አለኝ ከረጅም ጊዜ በኋላ ጎል አስቆጥሬያለሁ…
ከቀድሞው አዲስ ግደይ የተሻለውን አዲስ ግደይን ይዤ እቀርባለሁ ጥሩ ጊዜ ይኖረኛል ብዬ አምናለሁ
ሀትሪክ :- ከሰሞኑ መነጋገሪያ የነበረው ጎል አስቆጥረህ ያሳየኧው ምልክት ነው …ጥቂት የማይባሉ ደጋፊዎች የኢትዮጵያ ቡና ምልክትን ዘቅዝቀህ አሳይተሃል ይሉሃል … ምን ምላሽ አለህ ..?
አዲስ :- የኢትዮጵያ ቡና ክለብ፣አባላትና ደጋፊዎችን ይቅርታ እጠይቃለሁ ይህን አይነት ቅሬታ በውስጣቸው ስለፈጠርኩ…ምናልባት ግን ምልክቱን ሳሳይ የሚያውቁኝ
ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስጫወት ነበር.. ነገር ግን ለሲዳማ ቡና ስጫወትና ግብ ሳስቆጥር ምልክቱን ሳሳየው ኖሬያለሁ.. …ማንም ግን ተናግሮኝ አያውቅም .. ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ካላቸው የከተማ ተቀናቃኝነትና የደርቢ ስሜት አንጻር መበሻሸቂያ አድርገውት ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ.. የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በፎቶዬ ሲጠቀሙ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እልህ ሊጋቡ እንደሚችሉ መገመት አያቅተኝም። ምልክቱ ግን ከኢትዮጵያ ቡና አርማ ጋር የሚሄድበት ምክንያት የለም ..ለሲዳማ ቡና ስጫወት ሶሻል ሚዲያው እንደ አሁኑ አልበረከተም… ትኩረትም አያገኝም…ከበፊት ጀምሬ በተለይ ከሲዳማ ቡና ተሰላፊነቴ ጀምሮ እንደማደርገው ማወቅ አለባቸው ለተፈጠረው ግን የኢትዮጵያ ቡና ደፊዎችን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
.
ሀትሪክ :- የምታሳየው ምልክት ትርጉሙ ግን ምን ይሆን ….?
አዲስ :- ምልክቱን በተመለከተ ምክንያቱን ላልተረዱ ደጋፊዎች መናገር እፈልጋለሁ …. ለኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ክብር አለኝ ይህን የሚያደርግ ሰብዕናም የለኝም… በጭራሽ አላደርግም.. በዋናነት ግብ አስቆጥሬ ማሳየትን የፈለኩት የፍቅረኛዬ ስም መነሻ ፊደል ነው ፊደሉ ኤም ሲሆን የፍቅረኛዬ ስም መነሻ ስለሆነ ፍቅሬን ለመግለጽ ነው….። የፍቅር ምልክቴ እንጂ ኢትዮጵያ ቡናን ለማንቋሸሽ ያደረኩት አይደለም የተከፉት ደጋፊዎች እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ.. አሁን የምሰለፈው ማሊያውንም የማደርገው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው። ኢትዮጵያ ቡናን የማበሽቅበት ምክንያት የለም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግብ አስቆጥሬ ደስታዬን ስገልጽ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችን የማብሸቅበት ምክንያት የለም የኢትዮጵያ ቡናና የቅዱስጊዮርጊስ ደጋፊዎች ሲበሻሸቁ ስሜ ሊጠራ ይችላል ግን የኔ ሀሳብም አይደለም ይህን የሚፈጥር ህሊናም የለኝም
ሀትሪክ :-ለደጋፊዎቹ የመጨረሻ መልዕክት ካለህ..?
አዲስ :- ተቃውሞው ሰደበን ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ… ግን አልተሳደብኩም ነገ ለብሄራዊ ቡድን ስጫወት ግብ አስቆጥሬ ምልክቱን ባሳይ ብጨፍር ቅሬታ ሊነሳ ነው …? ለእኔ ግን አልተመቸኝም …ምልክቱ ለፍቅረኛዬ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ ብቻ ነው …ሌላ ትርጉም የለውም ..
ሀትሪክ:- አመሰግናለሁ..
አዲስ:- እኔም አመሰግናለሁ