ዲዲየ ጎሜዝ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሁለት ዓመት እሚያቆየውን ውል አራዝሟል ።
ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያሳለፍነውን ዓመት መቆየት የቻሉት ዲዲየ ጎሜዝ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የውል ስምምነታቸውን ለቀጣዩ ሁለት ዓመታት ማራዘማቸው ታውቋል።
አሰልጣኙ ያሳለፈውን ዓመት 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የቆዩት አሰልጣኙ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለቀጣዩ ሁለት ዓመታት እስከ ሐምሌ 2013 ዓ.ም ድረስ እሚያቆያቸውን ውል ፈርመዋል።
በአዲስአበባ ከተማ ዋንጫ ላይ እሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና በመክፈቻ ጨዋታው አዳማ ከተማን እሚያስተናግድ ይሆናል