የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ተራዘመ።
ነገ ቅዳሜ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል።
ምርጫዎ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ ለመወያየት የፊፋ ልዑክ መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣ ተገለጸ ።
የፌደሬሽኑ ጊዜያዊ ዋና ጸሐፊ አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ለሀትሪክ ድህረ-ገጽ እንደገለጹት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማህበር ፊፋ ረቡዕ ዕለት ለፌደሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አማካኝነት ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፈነው ጥር ወር ምርጫው የሚካሄድበትን ቀን ለካፍና ለፊፋ አስቀድሞ ባለማሳወቁ ምክንያት ምርጫው ሊራዘም መቻሉ ፊፋ በላከው ደብዳቤ ማስታወቁን ገልጸዋል።
- ማሰታውቂያ -
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ ለመወያየት የፊፋ ልዑክ መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣም ጠቁመዋል።
የፊፋ ልዑክ በምርጫው ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ ምርጫው የሚካሄድበትን ቀን ይፋ እንደሚደረግ ነው አቶ ሰለሞን ያብራሩት።