ሰሞኑን በተሰጠው የዳኞች ኩፐርቴስት ውጤት መሰረት በያዝነው አመት በኢንተርናሽናል መድረክ በአርቢርትነት የሚመሩ አርቢተሮች ይፋ ሆነዋል።
በዚህም መሰረት አርቢትር ሃይለየሱስ ባዘዘው ለአንድ ዓመት ከኢንተርናሽናል መድረክ ከራቀ በኃላ አርቢትር ዳዊት አሳምነው በመተካት ተመልሷል።
በተጨማሪ በረዳት አርቢተርነት ረዳት አርቢትር ፋሲካ የኋላሸት ረዳት አርቢትር ሃይለራጉኤል ወልዳይን፣ረዳት አርቢትር ይበቃል ደሳለኝ ረዳት አርቢትር ክንፈ ይልማን ቦታ እንዲተኩ ተወስኗል።በመጀመሪያ ፈተና የወደቁት ሊዲያ ታፈሰና አማኑኤል ሃይለስላሴ የድጋሚ ፈተና እድላቸውን በመጠቀም በቀጣዩም አመት ኢንተርናሽናል አርቢትር ሆነው መቀጠላቸውን አረጋግጠዋል።