የሊጉ ግርጌ ላይ ሚገኘው ደደቢት ተጨዋቾቹ የ4 ወር ና ከዚያ በላይ ደሞዝ አለመከፈላቸውን ተከትሎ የዛሬ መደበኛ ልምምዳቸውን ሳይሰሩ ቀርተዋል።ከጥቂት ሳምንታት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ደሞዝ አልተከፈለንም በሚል ለ3 ቀን ልምምድ ያቋረጡት የደደቢት ተጫዋቾች ፣ ችግር ውስጥ እሚገኘው የደደቢት እግርኳስ ቡድን እንከፍላችዋለን በሚል የተስፋ ቃል ልምምድ እንዲጀምሩ ቢያደርጉም ቃል የተገባላቸው ደሞዝ እስካሁን ስላልተከፈላቸው በድጋሜ ዛሬ ልምምድ አቋርጠዋል።
በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በሜዳው በፋሲል ከነማ በሰፊ የግብ ልዩነት ሽንፈት ያስተናገደው ደደቢት ላለመውረድ ያለው እድል ተራራን መግፋት ያህል ከባድ ሆኖበታል።