በ22ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት እና ሲዳማ ቡና ሲያሸንፉ ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በድሬዳዋ ከተማ ተሸንፏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳው ውጭከወላይታ ድቻ ጋር ተጫውቶ 1 ለ 1 አቻ ተለያይቷል፡፡
ፈረሰኞቹ ከሜዳቸው ውጭ ነጥብ ተጋርተው ቢመለሱም በግብ ክፍያ በልጠው በ39 ነጥብ ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
- ማሰታውቂያ -
በአዲስአበባ ስታዲየም ቀደም ብሎ የተጀመረው ጨዋታ ደደቢት አዲስ አበባ ከተማን አስተናግዶ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነጥብ ተስተካክሎ በጎል ክፍያ ተበልጦ በ2ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል፡፡
በጨዋታው ጌታነህ ከበደ በ25ኛ እና በ27ኛ ደቂቃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሮበን ኦባማ በ30ኛ ደቂቃ ሶስተኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል፡፡
ሲዳማ ቡና በበኩሉ ወልድያ ከተማን በይርጋለም ስታዲየም አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት እኩል 39 ነጥብ በመሰብሰብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ለሲዳማ ቡና ሙለዓለም መስፍን እና ላኪ ሳኒ፤ ለወልድያ ከተማ ደግሞ አንዱዓለም ንጉሴግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ድሬ ላይ 10ሰዓት የጀመረው ከባድ ሙቀት የነበረበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በድሬዳዋ ከተማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል ለድሬዳዋ ከተማ በ2ኛው እና በ9ኛው ደቂቃ ላይ ሐብታሙ ወልዴ እዲሁም በ64ኛ ደቂቃ ዘነበ ከበደ ሲያስቆጥሩ ለኢትዮጵያ ቡና ከዜሮ ከመሸነፍ የዳነበትን ጎል መስኡድ መሀመድ አስቋጥሯል ፡፡
ፋሲል ከነማ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ጅማ አባ ቡናን ያስተናገደበት ጨዋትም በፋሲል 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ለፋሲል ከነማ አብዱራህማን ሙባረክ እና ሙሉቀን ታሪኩ ግቦቹን ከመረብ ያሳረፉ ሲሆን የጂማ አባ ቡናን አንድ ግብ መሃመድ ናስር ነው ያስቆጠራት፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከሜዳው ውጭ አርባምንጭ ከተማን ገጥሞ በፒተር ኑዋድኬ እና በጂብሪል አህመድ ግቦች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በፍፁም ገብረማርያም ሁለት ግቦች እና በኢብራሂም ፉፋ አንድ ተጨማሪ ግብ መከላከያን 3 ለ 0 ረትቷል፡፡
በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 21 | 19 | 39 |
2 | ደደቢት | 22 | 14 | 39 |
3 | ሲዳማ ቡና | 22 | 7 | 39 |
4 | ኢትዮጵያ ቡና | 22 | 9 | 35 |
5 | አዳማ ከተማ | 22 | 4 | 35 |
6 | ፋሲል ከተማ | 21 | 1 | 32 |
7 | አርባምንጭ ከተማ | 22 | 1 | 29 |
8 | ሀዋሳ ከተማ |
22 | 2 | 28 |
9 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ |
22 | 2 | 27 |
10 | ወልዲያ ከተማ | 22 | -1 | 27 |
11 | ድሬዳዋ ከተማ |
22 | -6 | 25 |
12 | መከላከያ |
21 | -3 | 24 |
13 | ጅማ አባቡና | 22 | -4 | 23 |
14 | ወላይታ ድቻ |
22 | -10 | 23 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
22 | -13 | 19 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 22 | -12 | 16 |