_________________________________
ለቀጣይ ዓመት ውድድር ቡድናቸውን በማዘጋጀት የተጠመዱት ፒንቶ ኣብዱልከሪም ኒኪማ፣ሪቻርድ ኣፒያ እና ኣማራ ማሌን ኣሰናብቷል።
ላለፋት ሁለት ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ዘንድ ተወዳኝነትን ያገኘው ቡርኪናፎሲያዊው ኣብዱልከሪም ኒኪማ ጊዮርጊስ ቤት መልቀቁ እውን ሊሆን ችሏል።በፒንቶ ቡድን ከኣጥቂ ጀርባ በመሰለፍ የኣሰልጣኙ ኣንደኛ ተመራጭ የነበረው ኒኪማ ክለቡ ሊያቆየው ኣለመፈለጉ ግርምትን የፈጠረ ሆኗል እንዲሁም ኣምና በሁለተኛው ዙር በድኑን የተቀላቀሉት የፊት ኣጥቂዎቹ ኣማራ ኣሊና ሪቻርድ አፒያ ሌሎች ከጊዮርጊስ የተሰናበቱ ተጫዋቾች ናቸው።በጉዳት ብዙም ኣገልግሎት ያልሰጡት ሁለቱ ኣጥቂዎች የጌታነህ ከበደ እና አቤል ያለው መፈረም ተከትሎ በፈረሰኞቹ ቤት ተፈላጊነታቸው ሊቀንስ ችሏል።
ቅዱስ ጊዮርጊስን ላለፋት ሰባት ዓመታት በወጥ ኣቋም እያገለገለ ሚገኘው ግዙፋ ኡጋንዳዊው ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዱንካራ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እስከ መስከረም 30 2018 ሚቆይ ኮንትራት ያለው ቢሆንም ጊዮርጊሶች ሊለቅ ይችላል የሚል ስጋት ስላላቸው ዛሬ ከምዕራብ ኣፍሪካ ለሙከራ ግብ ጠባቂ እንደሚያመጡና የተሳካ ሙከራ ሚያሳልፍ ከሆነ ፈረሰኞቹን ሚቀላቀል ይሆናል።