የተጨዋቾችን ውል በማራዘም ላይ ሚገኙት ባህርዳር ከተማ የክረምቱ የመጀመርያ ፌርማውን አካሂዷል።ፋሲል ተካልኝን በእሰልጣኝነት የቀጠረው ባህርዳር ከተማ ሳሙኤል ተስፋዬን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ማስፈረም ችሏል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ኣካዳሚ ውጤት የሆነው ሳሙኤል ተስፋዬ የቀድሞ እሰልጣኙን መንገድ በመከተል የጣና ሞገዶቹን ተቀላቅሏል።በተያያዘ ዜና ባህርዳሮች ሌላው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች የሆነውን ፍሬዘር ካሳን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል።