የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ከፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማህበር ጋር በመሆን የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች አሰልጣኞች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ዛሬ ጥር18/2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም መስጠት ተጀመረ፡፡ስልጠናው ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር በተላኩ ሁለት ሙያተኞች አማካኝንት በመሰጠት ላይ ሲሆን፤ ስልጠናው ለ5ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
ስልጠናውን በማስተባበር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ልማት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ኩሩ ስልጠናውን አስመልክቶ የሚከተለውን አስተያየት ሰጠውናል “ ይህ ስልጠና ሰልጣኞች ከዘመናዊው እግር ኳስ ጋር ያላቸውን ቁርኝት የሚያሳድግ ብሎም ክለቦች በምን ምንገድ ራሳቸውን በውድድር ውስጥ ወጥነት ባለው መልኩ መወዳደር እንደሚችሉ የሚያሳይ በተግባር እና በንድፈ ሀሳብ የታገዘ ስልጠና ሲሆን በዚህ ስልጠና 36 አሰልጣኞች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ” ይህንን ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙት ሚስተር ሌስ ሐው እና ሚስተር ፒተር አጉስቲን (International and Regional coaching instructors) ናቸው፡፡