በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጥሩ ጅማሮን ማድረግ የቻሉት አዳማ ከተማዎች ከ ኮከብ ተጫዋቾቻቸው እንዲሁም ከአሰልጣኛቸው አሸናፊ በቀለ ጋር መለያየታቸው ይታወሳል ።
ይህንንም ተከትሎ አዳማ ከተማዎች በጅማ አባ ጅፋር የአንድ ዓመት ቆይታን ያደረጉትን አሰልጣኝ ፓውሎስ ጌታቸው ( ማንጎ ) ለመቅጠር መቃረባቸው ተሰምቷል ።
አዳማ ከተማ ሊጉ በኮሮና ቫይረስ እስከ ተቋረጠበት ድረስ በ ሀያ ሁለት ነጥቦች ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ይገኙ ነበር ።