ሰርቢያዊዉን ሰርዲያን ዚሂቮሆቭን አሚታወስአሰልጣኝነት የቀጠሩት ፈረሰኞቹ ሃይደር ሸረፋን ከመቐለ 70 እንደርታ አስፈርመዋል።
መቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫን እንዲያነሳ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካበረከቱት ተጨዋቾች ተርታ ሚጠቀሰው የመሃል ሜዳ ተጨዋቹ ሃይደር ሸረፋ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመቀላቀል ተስማምቷል።
የቀድሞው የጅማ አባቡና እና የደደቢት ኣማካኝ ሃይደር ሸረፋ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አብርሃም መብራህቱ ጥሪ ተደርጎለት ከጅቡቲ አንዲሁም ከሌሴቶ ጋር በተደረጉት ጨዋታዎች መጫወት ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ፈረሰኞቹ ከዚህ ቀደም የዓብስራ ተስፋዬና ኣቤል አንዳለ ከደደቢት፣ደስታ ደሙን ከወልዋሎ ማስፈረማቸው እሚታወስ ነው