*….. የዘጠኝ ተጨዋቾችና የአንድ አሰልጣኝ ደመወዝ አልከፈለም ተብሏል….
ወልቂጤ ከተማ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔን በሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የ9 ተጨዋቾችን ቀሪ ደመወዝ ባለመክፈሉ መታገዱ ታወቀ።
ወልቂጤ ከዘጠኙ ተጨዋቾች ውጪ የአሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙን ጨምሮ የኤፍሬም ዘካሪያስ፣ አንዋር ዱላ፣ ብርሃኑ ፋዲጋና አስራት መገርሳን ጨምር የዘጠኝ ተጨዋችችን ደመወዝ እንዲከፍል በ21/2/2016 ውሳኔ ቢሰጥም ክለቡ ውሳኔውን ተፈጻሚ ባለማድረጉ ከቀጣዩ የዝውውር መስኮት ጀምሮ ከዝውውር መስኮት መታገዱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
በሌላ ዜና የአዳማ ከተማ እግርኳስ ክለብ በ2011 የክለቡ ተጨዋቾች ሆነው ደመወዝ አልተከፈለንም ያሉትን ተጨዋቾች ሙሉ ክፍያ ማጠናቀቁ ታውቋል። ክለቡ የአምናና የዘንድሮ ተጨዋቾች ያልተከፈለ ክፍያ እንዳለበት ግን ታውቋል።