*…..እሰካሁን 18 ተጨዋቾች ውል አድሰዋል ክለብ
ቀይረዋል…..
የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ ሰአታት በቀሩበት በአሁኑ ሰአት በመስኮቱ የተጠቀሙ ክለቦችና ተጨዋችች ቁጥር ጨምሯል።
እስከ ትላንት ድረስ የነበሩት ክለቦች ቁጥር ሁለት
/ ፋሲል ከነማና ኢትዮ ኤሌክትሪክ/ ብቻ የፈረሙትም ተጨዋችች 3 ውል ያራዘመ አንድ ተጨዋች ብቻ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዝውውር መስኮቱ ተጠቅመው ራሳቸውን ያጠናከሩ ክለቦች ቁጥር ወደ አምስት ሲደርስ ዝውውር ያደረጉትም ተጨዋቾች ቁጥር 18 ደርሷል።
- ማሰታውቂያ -
በዚህ መስኮት በርካታ ተጨዋች ያስፈረመው ለገጣፎ ለገዳዲ ሲሆን አዲሱን አልጣኝ ዘማሪያም ወ/ ጊዮርጊስን ጨምሮ ሰባት ተጨዋቾችን ዝውውር ፈጽሟል። በዚህም መሠረት ኤሊያስ አታሮን ከሀድያ ሆሳዕና ፣ተስፋዬ ነጋሽን ከፋሲል ከነማ /በውሰት/፣ ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስን ከወልቂጤ ከተማ፣ ሱራፌል አወልን ከጅማ አባጅፋር፣ ዘነበ ከድርን ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ጋናዊውን ኮፊ ሜንሴህን አስፈርሟል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክም 6 ተጨዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን አማራ በቀለና አብዱራህማን ሙባረክን ከድሬዳዋ ከተማ፣ ነጻነት ገ/መድንን ከወላይታ ድቻ ፣ዮናስ ሰለሞንን ከሱዳን ቺካታራ ቺሶምን ከናይጄሪያ ሲያስፈርም የማታይ ሉልን ውል አድሷል። ሲዳማ ቡና ደስታ ደሙን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ህንዳዊው ፊሊፕን አስፈርሟል። አርባምንጭ ከተማ ዮሀንስ ተስፋዬን ከቤንች ማጂ አበበ ጥላሁንን ከኢትዮጵያ ቡና ሲያስፈርም ፋሲል ከተማም ዱላ ሙላቱን ከጅማ አባጅፋር ማስፈረሙ ታውቋል።
የዝውውር መስኮቱ ለሊት 6 ሰዓት ሳይዘጋ የሌሎች ተጨዋቾች ዝውውር ይካሄዳል ተብሎም ይጠበቃል።