በአስራ ሁለት ክለቦች መሀከል በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተዉ የትግራይ ዋንጫ ዉድድር በመቀሌ 70 እንደርታ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ዛሬ በተካሄደዉ የፍፃሜ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ እና ስሁል ሽረ የተገናኙ ሲሆን መደበኛዉ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1-1 በሆነ አቻ ዉጤት ተጠናቆ በተሰጠ የመለያ ምት መቀሌ 70 እንደርታ 6-5 በሆነ ዉጤት አሸንፎ የ2015 ዓ.ም የትግራይ ዋንጫ አሸናፊ ሆኖ ዉድድሩ ተጠናቋል።