የእለቱ ጨዋታ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ ሲጀመር የጨዋታው የመጀመሪያዎቹ ደቂቃ እንቅስቃሴዎች በፈጣን አጨዋወት ነበር የተጀመሩት።
ገና በጨዋታዉ ጅማሬ አርባምንጭ ከነማዎች በአህመድ ሁሴን በኩል ለጎል የቀረበ ኳስ መሞከር ቢችሉም በሲዳማ ቡናዉ ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ኦቮን ተመልሶበታል።
እንዲሁም በሲዳማ ቡናዎች በኩል ይገዙ ቦጋለ አከታትሎ ለጎል የቀረበች የሞከራት ኳስ በጨዋታዉ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሙከራ ሆና የተመዘገበች ናት።
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታዉ በተጀመረ በ18ኛ ደቂቃ አርባምንጭ ከተማዎች በአህመድ ሁሴን በኩል መሪ መሆን የቻሉበትን ጎል አስቆጥረዉ ጨዋታዉ ወደ 1-0 አመራ።
ሲዳማ ቡናዎች ጎል ከተቆጠረባቸዉ በኋላ የጨዋታዉን ዉጤት ለመቀየር ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም እስከ መጀመሪያዉ የጨዋታ ክፍለ ግዜ አጋማሽ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ድረስ ጎል ማስቆጠር ሳይችሉ ጨዋታው ቢቀጥልም የመጀመሪያዉ አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሽርፍራፊ ደቂቃዎች ቀርተዉ እያለ የአርባምንጭ ከተማዎቹ አሸናፊ ፊዳ በእራሱ ላይ ባስቆጠረዉ ጎል የመጀመሪያው አጋማሽ 1-1 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።
ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡናዎች አቤል እንዳለን በሙሉቀን አዲሱ ቀይረዉ የገቡ ሲሆን የሁለተኛዉ አጋማሽ በሁለቱም ቡድን በኩል እንብዛም የጎል ሙከራ ያልተስተዋለበት ሲሆን በ80ኛ ደቂቃ ላይ ሲዳማ ቡናዎች ቅጣት ምት ኳስ አግኝተዉ አበባየው ዮሐንስ ሲያሻማ አጃህ ጨረፍ አድርጓት በግቡ የላይኛው አግዳሚ የተመለሰችበት ኳስ የሁለተኛዉ አጋማሽ ለጎል የቀረበች ኳስ ሆና ተጠቃሽ ናት።
ከእዛ በኋላ በሁለቱም ቡድን በኩል እንብዛም ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ሳንመለከተ የእለቱ ጨዋታ 1-1 በሆነ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል።
ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ሲዳማ ቡና ከደረጃዉ ላይ አንድ በማሻሻል በ35 ነጥብ ወደ 9ኛ ደረጃ ከፍ ሲል አርባምንጭ ከነማዎች በበኩላቸዉ ያላቸዉ 29 ነጥብ ላይ 1 በመጨመር በ30 ነጥብ እዛሁ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።