መድንን ውጤታማ ያደረጉት አሰልጣኝ ገ/መድን ሃይሌ አዲሱ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል ።
አሰልጣኙ ከፌዴሬሽኑ ጋር በተስማሙት መሰረት የአንድ አመት ውል የፈረሙ ሲሆን ከ250 ሺህ የተጣራ ደመወዝ ጋር የስልክ ፣ የነዳጅ ፣ የማትጊያ ፣ የህክምና ወጪ የሚቻል ይሆናል ። ከዚህም ውጪ የውጪ ጉዞ በቢዝነስ ክላስ የሚያዝለት ሲሆን ራስን የማብቃት አላማ ያለው የትምህርት ወጪውን ፌዴሬሽኑ የሚሸፍን ይሆናል።
በጉዳዩ ዙሪያ ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንደተናገሩት የቀድሞ አሰልጣኝ ከተሰናበቱ በኋላ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቀጣዩ አሰልጣኝ ገብረ መድን ሃይሌ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ያስተላለፈው የዛሬ 5 ወር አካባቢ ነው አምና ደግሞ መድን ለዋንጫ እየተፎካከረ ስለነበር አሰልጣኙን ለማናገር አልተቻለም ከክለቡ መድን ጋር ስናወራ ቆይተን ክለቡ የያዘው ፕሮጀክት ሰፊ በመሆኑ እዚያ እየሰራ ብሄራዊ ቡድነን እንዲይዝ አናግረን ተስማምተናል” ሲሉ አስረድተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ዋና ስራ አስፈጻሚው እንዳሉት ” አሰልጣኙ ጠንካራና ተፍካካሪ ለቻን ፣ ለአፍሪካና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ውጤታማ ቡድን መፍጠር ..አጭርና ረጅም እቅድና ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅበታል የሁለቱም ወገኖች ውል ሲቋረጥ በሁለቱም ስምምነት ፣ መለያየቱን ፌዴሬሽኑ ከፈለገ ለአሰልጣኙ የ5 ወር ደመወዝ መክፈል
በተቃራኒው አሰልጣኙ መለያየት ከፈለጉ 5 ወር ከፍለው እንዲወጡ ተስማምተናል” ሲሉ ውሉን አብራርተዋል።
አሰልጣኙ ገ/መድን ሃይሌ በበኩላቸው “ስድስት አመት ቢያልፈውም አሁን ወደሃላፊነት ስመጣ ለ2ኛ ጊዜ ነው… ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት የሰራሁበት ይህን ሃላፊነቱን በደስታ ተቀብያለሁ ቡድናችን በፈጣን እንቅስቃሴ ውስጥ የመጫወት አቅም ያንሰዋል በዚህ ድክመት ላይ አተኩረን የምንሰራ ይሆናል ባለው ፕሮግራም መሠረት ስራዬን ዛሬ ጀምሬ የምሰራ ይሆናል..ለውድድሩ የሚሆኑ ተጨዋቾች ስም ዛሬ ማታ ይፋ ይደረግና ሆቴል ገብተው እሁድ ልምምድ የሚጀምሩ ይሆናል” ሲል ተናግሯል።