በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት 3ኛ ቀን ውሎ በቀዳሚነት ወላይታ ድቻን ከ አዲስ አበባ ከተማ አገናኝቶ ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰኮንዶች ሲቀሩት በተቆጠረ ግብ የጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል ።
በ10ኛው ሳምንት በጅማ አባጅፋር የተሸነፉት አዲስ አበባ ከተማዎች በጨዋታው ከነበረው ቋሚ አሰላለፍ ሶስት ቅያሪዎችን ያደረጉ ሲሆን በብዙአየሁ ሰይፉ ፣ ሙሉቀን አዲሱ እና እና ሪችሞንድ ኦዶንግ ምትክ ኤልያስ አህመድ ፣ ቻርለስ ሪባኑን እና የሽዋስ በለው ተክተው ሲያስገቡ በወላይታ ድቻ በኩል አርባምንጭ ከተማን ከረቱበት ጨዋታ አንድ ቅያሪ ብቻ በማድረግ በአናጋው ባደግ ስንታየሁ መንግስቱን ወደ ቋሚ አሰላለፍ መልሰዋል ።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አዲስ አበባ ከተማዎች ኳሱን ተቆጣጥረው በመጫወት የተሻሉ ሆነው የታዩ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል በረጃጅም እና ፈጣን ሽግግሮች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር የቻሉበት ነበር ።
- ማሰታውቂያ -
9ኛው ደቂቃ ላይ የሽዋስ በለው ከፍፁም ጥላሁን የደረሰውን ኳስ በሳጥን ውስጥ ቢሞክረውም ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወቷል ። በ20ኛው ደቂቃ ላይ ስንታነሁ መንግስቱ ከአንተነህ ጉግሳ በረጅም የደረሰውን ኳስ ተጠቅሞ የጦና ንቦቹን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሏል ።
32ኛ ደቂቃ ላይ የሽዋስ በለው ከሳጥን ውጪ ሞክሮቶ በግብ ጠባቂው የተመለሰበት ኳስ እና 39ኛ ደቂቃ ላይ ፍፁም ጥላሁን ሶስት የወላድቻ ተከላካዮችን በድንቅ ብቃት አለፎ ወደ ግብ የላከቅ ኳስ በግቡ ቋሚ ተመልሶ ደጉ ደበበ ወደ ውጪ ያወጣው ኳስ በአደጋማሹ በአዲስ አበባ ከተማ በኩል የታዩ የግብ ዕድሎች ነበሩ ።
በሁለተኛው አጋማሽ በመመራት ላይ የነበሩት አዲስ አበባ ከተማዎች ብልጫ ወስደው የታዩበት ነበር ። በዚህም 63ኛ ደቂቃ ላይ አዲስ አበባ ከተማዎች በጥሩ ቅብብል ወደ ሳጥን ይዘው የገቡትን ኳስ ጋናዊው አጥቂ ሪችሞንድ ኦዶንጎ አስቆጥሮ የጨዋታውን ውጤት ወደ አቻ ቀይሮታል ።
የጦና ንቦቹ መሪነታቸውን ለመመለሽ ተነቃቅተው በመጫወት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን ከግቡ መቆጠር አንድ ደቂቂበኋላ አዲስ ህንፃ ወደ ግብ የላከው ኳስ በግብ ጠባቂዝ ዳንኤል ተሾመ ተመልሶ የማዕዘን ምት ሆኗል ። 76ኛ ደቂቃ ላይ ሪችሞንድ ኦዶንጎ ከፍፁም ጥላሁን ያገኘዌን ኳስ በሳጥን ውስጥ ሆኖ አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ ግብ ጠባቂው ወንድወሰኝ አሸናፊ ደርሶ አውጥቶበታል ።
የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ አራት ደቂቃዎች ተጨምረው ሊጠናቀቁ የተወሰኑ ሰከንዶች ሲቀሩት አዲስ ህንፃ ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ ቃልኪዳን ዘላለም አስቆጥሮ ክለቡን አሸናፊ ማድረግ ችሏል ።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ነጥቡን 19 በማድረስ ወደ 3ኛ ደረጃ ከፍ ሲል አዲስ አበባ ከተማ በበኩሉ በ11 ነጥብ ባለበት 13ኛ ደረጃ ላይ የሚቆይ ይሆናል ።
በ12ኛ ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ድቻ መከላከያን አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን የሚገጥሙ ይሆናል ።