በአስራ አራተኛዉ ሳምንት ተጠባቂ መርሐግብር የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ቡድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ዲቻ ጋር መርሐግብሩን በአቻ ዉጤት ሲያገባድድ ፤ አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በተደረገ መርሐግብር ደግሞ
በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ዲቻ በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ተመጣጣኝ የሚባል የጨዋታ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የተስተዋለ ሲሆን ፤ በሙከራ ረገድም ድንቅ የሚባሉ ሙከራዎችን መመለክት ተችሏል ለአብነት በመጀመሪያው አጋማሽ በ24ኛዉ ደቂቃ ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች ዳግማዊ አርአያ ከቢኒያም የተቀበለዉን ኳስ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂዉ በግሩም ብቃት አምክኖበታል።
በፊት መስመር ተጫዋቹ ሞሰስ ኦዶ እና ተከላካዩ ፍሪምፖንግ ሜንስ አማካኝነት ድንቅ ሙከራዎችን ያድርጉ እንጅ ሙከራዎቹ በግብ ዘቡ ቢኒያም ገነቱ ከሽፈዋል። በተቃራኒው እምብዛም ሙከራ ማድረግ የቻለዉ ወላይታ ዲቻ በ34ተኛዉ ደቂቃ ላይ በአጥቂዉ ቢኒያም ፍቅሬ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም በግብ ዘቡ ባህሩ አማካኝነት ከሽፏል።
ከዕረፍት መልስ ምንም እንኳን ፈረሰኞቹ የተሻሉ የነበሩ ቢሆኑም ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር በሙከራ ረገድ የተቀዛቀዘ የነበረ ሲሆን ፤ ነገር ግን ከሀያ አምስት ደቂቃዎች በኋላ ፈረሰኞቹ መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አግኝተዋል። በዚህም ከቀኝ መስመር በኩል ከሄኖክ የተሻገረለትን ኳስ ሞሰስ ኦዶ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን መሪ ማድረግ ችሏል። ግብ ከተቆጠረባቸው የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረዉ መጫወት የጀመሩት ዲቻዎች ከተደጋጋሚ ሙከራዎች በኋላ ጨዋታዉ ሊገባደድ በጭማሪ ደቂቃ ላይ ቢኒያም ፍቅሬ ከሳጥን ዉጭ ግብ አስቆጥሮ ክለቡን አቻ በማድረግ መርሐግብሩ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት እንዲጠናቀቅ አድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
በዕለቱ ሁለተኛ እና የሳምንቱ የመጨረሻ መርሐግብር ደግሞ ኢትዮጵያ መድን እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታቸዉን ያለ ግብ በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በአስራ ሶስተኛዉ ሳምንት ሽንፈትን አስተናግደዉ የነበሩት እና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ጥሩ የሚባል ፋክክርን ሲያስመለክቱን ያመሹት ሁለቱ ክለቦችበአመዛኙ መስመር ላይ ያተኮረን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የተስተዋለ ሲሆን በተለይ ምንም እንኳን በሙከራ ረገድ የተቀዛቀዘ ቢሆንም በ26ተኛዉ ደቂቃ ላይ ኢትዮጵያ መድን በመሐመድ አበራ ምክንያት ግብ አስቆጥረዉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኳሱ በዕጅ ተነክቷል በሚል ግቡ ተሽሯል። እምብዛም ሙከራን ባላስመለከተን የምሽቱ ጨዋታ መጨረሻ ላይም ወልቂጤ ከተማዎች በአጋማሹ መጨረሻ ላይ በሳምሶን ጥላሁን አማካኝነት ድንቅ የግብ ሙከራ አድርገዉ የነበረ ቢሆንም የግብ ዘቡ መሐመድ ኑራ አምክኖታል ።
ከዕረፍት መልስም በተመሳሳይ የተቀዛቀዘ እንቅሰቃሴን በተመለከትንበት ሁለተኛዉ አጋማሽ ሁለቱም ተጫዋቾች የተጫዋቾችን ለዉጥ አድርገዉ ወደ ሜዳ የገቡ ቢሆንም ጥሩ የሚባል ሙከራንም በ48ተኛዉ ደቂቃ ላይ ወልቂጤ ከተማዎች በራምኬል ሎክ አማካኝነት ድንቅ ሙከራን ያደረጉ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ አምክኖታል።
የወልቂጤ ከተማን የተሻለ የበላይነት እያስመለከተን በቀጠለዉ የሁለተኛዉ አጋማሽ ላይም በመጠናቀቂያዉ ወቅት በ82ተኛዉ ደቂቃ ላይ ጋዲሳ መብራቴ ድንቅ ሙከራ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ኳሱ ወደ ዉጭ ወጥቶበታል ፤ ሁለቱም ቡድኖች በሙሉ ዘጠና ደቀቃዉ ግብ ለማስቆጠር ያደርጉት የነበረዉ ጥረት ፍሬ ሳያፈራ ቀርቶ ጨዋታዉ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተጠናቋል።