የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ የካቲት 04 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አራቱ በመሸናነፍ ቀሪ አራቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች ተቆጥረዋል። 31 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል ።
በሳምንቱ በስምንት ተጫዋቾች ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ኤልያስ አህመድ(ድሬደዋ ከተማ) የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል እንዲሁም ኤርሚያስ ሹምበዛ(ኢትዮጵያ ቡና)፣ ምንይሉ ወንድሙ(መቻል) ፣ ኩሊባሊ ካድር (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ አስጨናቂ ፀጋዬ(ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን(ሲዳማ ቡና)፣ ጌታለም ማሙዬ(ሻሸመኔ ከተማ) እና እያሱ ለገሰ(ድሬደዋ ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቀቂያ የተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል ።
- ማሰታውቂያ -
በሁለት ክለቦች ላይም ተመሳሳይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፏል። ከድሬደዋ ከተማ ተጫዋቾች እያሱ ለገሰ፣አብዩ ካሣዬ፣ኤልያስ አህመድ ቻርልስ ሙሲጌ እና ኢስማኤል አብዱል ጋኒዩ እንዲሁም ከሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን፣ ብርሀኑ በቀለ፣ ማይክል ኪፖሩል፣ ዳመነ ደምሴ እና መክብብ ደገፉ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ሁለቱ ክለቦች የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡