*….አዲስ አበባ ድሬዳዋ ሀዋሳ…አሁን መካከለኛ ምስራቅ
በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢ ከቀናቶች በኋላ ዱባይ ላይ ይካሄዳል ተባለ።
ከ29 አመት በፊት በተመሰረተው በኒያላ ኢንሹራንስ ሙሉ ኢንሹራንስ የተገባለት የአምስት ቀኑ ፕሮግራም
ራት ግብዣ ፣ገቢ ማሰባሰቢያ የቀድሞ የክለቦቹ ማሊያ ሽያጭ የባህል ልውውጥ የሚኖርበት መሆኑ ታውቋል።
የቀድሞ የአርሰናልና የማን.ሲቲ ኮከብ ባካሪ ሲኛ በሚገኝበት ቦለርስ አካዳሚ ቀለል ያለ ልምምድ ሲሰሩ የክለቦቹ ማናጅመንት ደግሞ ከአካዳሚው ባለቤቶችና ባለሙያዎች ድጋፍና ሙያዊ ሽግግር በሚፈልጉበት መንገድ ዙሪያ ሚኒ ወርክሾፕ እንደሚያደርጉ ታውቋል።
በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የፊፋ ማች ኤጀንት በሆነው ኢንጂነር ፍጹም አድነው በሚመራው ተቋም ጥላ ውስጥ በሚካሄደው የሸገር ደርቢ በዱባይ መርሃ ግብር ለተጨዋቾቹ ከጫና አርፈውና ዘና ብለው የሚመጡበት የገቢ አቅማቸውን የሚያጠናክሩበት በዱባይና አካባቢው ከሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ጋር የሚገናኙበት በመሆኑ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው የሁለቱም ክለቦች አመራሮች ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
ተቋሙ ወደ አምስት ከተሞች በቀጣይ የመጓዝ እቅድ ያለው ሲሆን በአሜሪካ በደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ከኬንያ ተመሳሳይ የእኛ ጋር ኑ ጥያቄ መቅረቡ ታውቋል።
“ይሄ የሸገር ደርቢ ስያሜ ትልቅ ብራንድ ነው በመላው አለም መካሄድ አለበት እግርኳስ ደግሞ የወቅቱ ትልቅ ኢንዱስትሪ ነው መካከለኛ ምስራቅ ትልቅ የገበያ ምንጭ ነው ከነኚህ ጋር መቆራኘት ትልቅ ጥቅምና ዋጋ እለው” ሲሉ አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።
የቅዱስ ጊዮርጊሱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ”
ጉዞው ስኬታማ እንደሚሆን አረጋግጠናል ፍጹም አድነውን ላመሰግን እወዳለሁ ፕሮግራሙ ከክለብ በዘለለ የሀገራትን የሚያቀራርብ ነው ጊዜው እረፍት መሆኑ በዱባይ የሚገኙ የቀድሞ ደጋፊዎቻችንን ለማግኘት አዲስ ጥምረት ለመፍጠር ትልቅ ትርጉም አለው የክለባችንን ማሊያና ልዩ ልዩ ለሽያጭ የሚቀርቡ ቁሶችን ለመውሰድ አቅደናል ጉዞውም በቀጣይም እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ የኢትዮጵያ ቡናው አቻቸው አቶ ገዛኦኝ ወልዴ በበኩላቸው ” 3 አመት ሙሉ ምክንያቱ እግርኳስ ይሁን አይሁን ሳናውቅ የደርቢ ጨዋታውን ማካሄድ አልቻልንም ጉዞው ኢንተርናሽናል ግንኙነት ይፈጥርልናል የአካዳሚ አሰራር እንድናውቅ ደጋፊያችንን እንድናገኝ እንዲሁም ያሉንን ቁሳቁስ ለገበያ እንድናቀርብ ይጠቅመናል በዚህም ደስተኛ ነኝ ተጨዋቾች አርፈው ተዝናንተው ንጹህ ሆነው አርፈው
ለቀጣዩ ዙር ፍልሚያ እንዲዘጋጁ ያደርጋቸዋል የፕሪሲዝን ዝግጅት እንዴት ማድረግ እንደምንችልና ኢንተርናሽናል ግንኙነት እንዲኖረንም ይጠቅማል” ሲሉ ተናግረዋል።
የመርሃግብሩ ዋና ጠንሳሽ ኢንጂነር ፍጹም አድነው “ለዚህ ጉዞ ከጎኑ የቆሙትን ተቋማትና ግለሰቦችን አመሰግናለሁ የዚህ የሸገር ደርቢ ጉዞ ዋነኛ አላማ ከጥቅም በላይ የኢትዮጵያ እግርኳስን ኢንዱስትሪ ማነቃቃትና ከፍ ማድረግ ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።