በዛሬው ዕለት በተደረገው 43ኛው የለንደን ማራቶን በዜግነት ኔዘርላንላዊ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በመጀመሪያ የማራቶን ውድድሯ 2:18:33 በመግባት አሸንፋለች ።
የአትሌቷ አሸናፊነት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያስገኘላት ሲሆን በተለይም በውድድሩ ለሁለት ያህል ጊዜያቶ በህመም ምክንያት የምታቋርጥ በሚመስል መልኩ ወደ ኋላ ብትቀርም በመጨረሻም ራሷን ከፊት አግኝታለች ።
በወድድሩ የአምናው የለንደን ማራቶን አሸናፊዋ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ፣ አትሌት መገርቱ አለሙ ፣ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር እና አትሌት ሼልያ ቼፕኪሩይ ሲመሩ ቢቆዩም አትሌት ሲፋን ከኀላ በመድረስ በድንቅ አጨራረስ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች ።
አትሌት ሲፋንን በመከተል አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:18:37 ሁለተኛ ፣ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 2:18:53 ፣ አትሌት አልማዝ አያና በ2:20:44 እንዲሁም ታዱ ተሾመ በ2:21:31 ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
- ማሰታውቂያ -
በወንዶቹ ውድድር ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም በ2:01:25 በመግባት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጨምር አሸናፊ ሆኗል ።
የአለም ሻምፕየኑ አትሌት ታምራት ቶላ በ2:04:59 በሶስተኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ልዑል ገብረስላሴ በ2:05:45 እንዲሁም አትሌት ሰይፉ ቱራ በ2:06:38 በአምስተኝነት ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።