መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል
ሀዋሳ ከተማአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

በሶስተኛው ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለተኛ ጨዋታ አዳማ ከተማ በዳዋ ሆጤሳ ብቸኛ ግብ ሀዋሳ ከተማን ረቷል ።

በሀዋሳ ከተማ በኩል በሁለተኛው ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን በረቱበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ የሶስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ በሰለሞን ወዴሳ ፤ እዮብ አለማየሁ እና አዲሱ አቱላ
ምትክ ላውረንስ ላርቴ ፤ ብርሀኑ አሻሞ እና ኤፍሬም አሻሞን ሲያሰለፉ በአዳማ ከተማ በኩል በሳምንቱ መቻልን በረቱበት ጨዋታ ላይ በነበረው ምርጥ አስራአንድ ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ጨዋታውን ጀምረዋል ።

 

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ አዳማ ከተማዎች በተሻለ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል መድረስ የቻሉ ሲሆን የጠሩ የግብ ዕድሎችን ከመፍጠር አኳያ ግን ክፍተቶች ነበሩባቸው ። በአንፃሩ ሀዋሳ ከተማዎች ከራሳቸው የሜዳ ክፍል ለመውጣት እጅጉን ተቸግረው አብዛኛውን የአጋማሹን ክፍለ ጊዜ በመከላከል እንቅስቃሴ ላይ አሳልፈዋል ።

ለበርካታ ደቂቃዎች ያለ ግብ ሙከራ በመካሄድ ላይ የነበረው ፍልሚያ በ35ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያው የግብ ሙከራ ተስተናግዶበታል ።

ኤርትራዊው አሊ ሱሌማን ከመሀል የተላከለትን ኳስ ከሳጥኑ ጠርዝ ግራ አቅጣጫ ወደ ግብ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ኩዋሜ ባህ ግብ ከመሆን አድኖታል ።

በ42ኛው ደቂቃ አዳማ ከተማዎች ጥሩ የግብ ዕድል መፍጠር ችለው የነበረ ሲሆን ደስታ ዮሀንስ ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ አብዲሳ ጀማል በግንባር ገጭቶ የግቡ ቋሚ መልሶበታል ።

የመጀመሪያው አጋማሽም ያለ ግብ ተጠናቋል ።
በተመሳሳይ እንቅስቃሴ በቀጠለው የ ሁለተኛው አጋማሽ ሀይቆቹ በቀዳሚው አጋማሽ ከነበራቸው በተሻለ ለመንቀሳቀስ በመሞከር በተለይም ሙጂብ ቃሲምን ኢላማ ያደረጉ ኳሶችን ወደ ተጋጣሚያቸውን የግብ ክልል ለማድረስ ጥረዋል ።

ከሁለተኛው አጋማሽ መጀመር 15 ደቂቃዎች በኋላ አዳማ ከተማዎች ካልታሰበ ቦታ ግብ አግኝተዋል ።

የቡድኑ አምበል ዳዋ ሆጤሳ ከርቀት ወደ ግብ የመታው ኳስ በመድኅኔ ብርሀኔ ተጨርፎ የግብ ጠባቂው አላዛር ሽመልስ ቦታ አያያዝም ታክሎበት ግቡ ሊቆጠር ችሏል ።

ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ በሀዋሳ ከተማ በኩል ብርሀኑ አሻሞ ከቆመ ኳስ ያሻገረውን ኳስ አብዱልባሲጥ ከማል በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ለጥቂት ሳይሳካ ቀርቷል ።

በ70ኛው ደቂቃ ላይ ኤፍሬም አሻሞ ከግቡ ትይዪ የተገኘውን የቅጣት ምት አክርሮ ወደ ግብ መሞከር ቢችልም ኳሱ ኢላማውን መጠበቅ ሳይችል ቀርቷል ።

በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ሀዋሳ ከተማዎች ቅያሪዎችን በማድረግ የአቻነቱን ግብ ፍለጋ ለማግኘት ቢኳትኑም የአዳማ የኋላ መስመር ይህን የሚፈቅድ አልነበረም ።

በ78ኛው ደቂቃ ላይ ተከላካዩ ሚሊዮን ሰለሞን የአላዛርን አቋቋም ተመልክቶ ወደ ግብ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወቷል ።

ጨዋታው ሊጠናቀቅ የሰከንዶች ዕድሜ በቀሩት ጊዜ አዳማ ከተማዎች በመልሶ ማጥቃት ጥሩ ዕድል መፍጠር ቢችሉም ዳንኤል ደምሴ አጋጣሚውን ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

በመጨረሻም አዳማ ከተማ በዳዋ ሁጤሳ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፏል ።

በአራተኛው ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ጥቅምት 8(ማክሰኞ) አዳማ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 7:00 ላይ ሲገጥም 10:00 ላይ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ይጫወታል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...