*….ተጨዋቾቹ ተበድረው በከፈሉት ሰርቪስ ከአዳማ አዲስ አበባ መጥተዋል…
*…..ክለቡ ደግሞ ይታገሱን ችግሩን ለመፍታት እየጣርን ነው እያለ ነው……
ሃያ ሁለት የሀምበሪቾ ዱራሜ ተጨዋችች ከ4-6 ወር ደመወዝ አልተከፈለንም በማለት ክለባቸውን በይፋ ከሰሱ።
- ማሰታውቂያ -
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ 22 ተጨዋቾች ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ከአዳማ አዲስ አበባ በመምጣት
በተከራዩት ሰርቪስ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ቅሬታቸውን በደብዳቤ በማቅረብ ከዚህ በኋላ ለሚወስዱት ርምጃ ሃላፊነቱ የክለቡ መሆኑን ማሳወቃቸው ታውቋል።
ክለቡ ለተጨዋቾቹ ደመወዝ መክፈል ባለመቻሉ የተጨዋቾቹ ህይወት ችግር ላይ ሲሆኑ ቤት ኪራይና የልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ካለመቻላቸውም በላይ ቤተሰቦቻቸውን መምራትና ማስተዲደር እንዳልቻሉና ለበአል ቤተሰብ ጋር መሄድ ከብዷቸው አዳማ ባረፉበት ስፍራ በመቆየት በዓሉን ያሳለፉ ተጨዋቾች መኖራቸው ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳግም በሰጡት ምላሽ ” ምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ክልል እንደመሆኑ የበጀት እጥረት በመከሰቱ የተፈጠረ ነው የዞኑ አስተዳዳሪ ከሆኑት የክለቡ የበላይ ጠባቂ ጋር
ተነጋግረን ችግሩ እንደሚፈታ በመግለጻቸው ችግሩ እንደሚወገድ ተስፋ አደርጋለሁ ፕሪሚየር ሊጉ የሚፈልገው በጀት ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሀድያ ሆሳዕና ክለባችንን ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው የማድረግ ስራ በመስራት ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር የምንችለው ሁሉ ለማድረግ እንጥራለን ተጨዋቾቻችንም ይህን ተረድተው ይታገሱን ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ተጨዋቾቹ በቀጣይ ጨዋታ ይገባሉ ወይ የሚለው ጥያቄ ምላሽ ባያገኝም ሀምበሪቾ ዱራሜ በ3 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ በ12ኛ ሳምንት መርሃግብር የፊታችን ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር እንደሚጫወት ይጠበቃል።