ጨዋታዉ ከወትሮዉ በበለጠ መልኩ በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ መካሄድ የጀመረ ሲሆን ሲዳማ ቡናዎች በጨዋታው ጅማሬ ገና በ2ኛ ደቂቃ በደስታ ደሙ በኩል ባስቆጠሩት ጎል በጠዋቱ መሪ ሆነዉ ጨዋታዉ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ፋሲል ከነማዎች ከተቆጠረባቸዉ ጎል በኋላ የመሀል ክፍሉ ላይ ጠንክረዉ በመጫወት ወደ ሲዳማ የግብ ክልል ለማምራት ሙከራዎችን ሲያደርጉ ነበር።
ሲዳማ ቡናዎች ካስቆጠሩት ጎል በኋላ አልፎ አልፎ ከሚጫወቱት የመልሶ ማጥቃት ተሻጋሪ ኳሶች ዉጪ የጀርባ ክፍላቸዉን አጠናክረዉ መከላከልን አዘዉትረዉ የተጫወቱ ሲሆን ፋሲሎች በበኩላቸዉ ወደ ሲዳማ የሜዳ ክፍል በተደጋሚ በማምራት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ለመሞከር ጥረት ያደረጉ ሲሆን ነገር ግን የሲዳማዎች የተከላካይ ክፍል እና በረኛዉ ፈተና እንደሆነባቸዉ የመጀመሪያዉ አጋማሽ 1-0 በሆነ ዉጤት ተጠናቀቀ።
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛዉ አጋማሽ ሲዳማ ቡናዎች ቅያሪ አድርገዉ ሙሉቀን አዲሱን ይዘዉ ሲገቡ ፋሲሎች በበኩላቸዉ ኦሴ ማዉሊን ይዘዉ ገብተዋል።
ሁለተኛዉን አጋማሽ ፋሲሎች ተጭነዉ መጫወት የጀመሩ ሲሆን የሲዳማ ቡና የግብ ክልል ዉስጥ በተደጋጋሚ በመድረስ ለሲዳማዉ በረኛ ፈተና የሆኑበት ሲሆን በግብ ጠባቂዉ የተመለሰባቸዉ ለጎል የቀረቡ ኳሶች ተጠቃሽ ነበሩ።
ሲዳማዎች ከፋሲሎች ተሻግረዉ የሚመጡ ኳሶችን በመልሶ ማጥቃት ወደ አጥቂያቸዉ ፍሊፕ አጃህ ዘንድ ኳሶችን በተደጋጋሚ ሲያደርሱ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የፋሲል ተከላካዮች ሊበገሩ አልቻሉም ነበር።
ፋሲል ከነማዎች የመጨረሻዎቹን ደቂቃዎች አቻ ሊወጡ የሚችሉበትን ዉጤት የሚያገኙበትን እድል በኦሴ ማዉሊ በኩል አግኝተዉ የነበረ ቢሆንም የጎሉ የላይኛዉ የግዳሚ መልሶበት ኳሷ ወደ ዉጪ ወታለች። እንዲሁም ናትናኤል ከሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ ፍሊፕ ኦቫኖ ጋር ተገናኝቷ ኳሷ በግብ ጠባቂዉ የተመለሰችበት አጋጣሚ በፋሲሎች በኩል ቁጭትን የሚጭር ሆኖ ነዉ ያለፈዉ።
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፋሲሎች የጎል እድል ለመፍጠር ደጋግመዉ ወደፍለፊት በማመዘን ለመጫወት የሞከሩ ቢሆንም ነገር ግን ሳይሳካላቸዉ ቀርቶ ጨዋታዉ በሲዳማ ቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ሲዳማ ቡና ደረጃዉን በማሻሻል ወደ ወደ 10ኛ ደረጃ መቷል።