መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የፕሪሚየር ሊጉን ቀጣይ ጨዋታዎች የሚያስተናግዱ ከተሞች ይፋ ተደርገዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፕሪሚየር ሊጉን ቀጣይ ጨዋታዎች የሚያስተናግዱ ከተሞች ይፋ ተደርገዋል

አጋራ
አጋራ

የ2015 ዓ.ም የውድድር ዘመን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቀጣይ ጨዋታዎች የሚደረጉባቸው ስታዲየሞች በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርገዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የሶስት ከተሞችን(ባህር ዳር፣ አዳማ እና ሃዋሳ) ዝግጅት ከጎበኘ በኋላ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ቀጣይ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የሚደረግባቸውን ስታዲየሞች ለይቷል ።

ከአክሲዮን ማህበሩ በተላኩ ልኡካን ቡድኖችም የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የሃዋሳ ዩነቨርስቲ ስታዲየሞች ተገምግመዋል ።

በዚህም መሰረት ከ17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እስከ 27ኛ ሳምንት ውድድሩ በቅደም ተከተል በመጀመሪያ በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እና በቀጣይ ደግሞ በሃዋሳ ከተማ በሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም እንዲደረጉ ተወስኗል ።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2015 የወድድር ዘመን እስከ 17ኛው ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ድረስ በድሬደዋ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን የ17ኛው ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎችና ከ18ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ መልስ የሚደረግ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...