የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር ከዲ ኤስ ቲቪ ጋር በመነጋገር በቀጣይ የሚደረጉ የፕሪሚየር ሊጉ ውድድሮች ላይ ትንተና የሚሰጡ 10 ተጫውተው ያለፉትን ባለሙያዎች መመረጣቸውን ይፋ አድርጓል።
ማህበሩ ከጥር 18-20 ባሉት ሁለት ቀናት ባወጣው የማስታወቂያ በጨዋታዎቹ ላይ ትንተና ለመስጠት ፍቃደኛ የሆኑ ተጫውተው ያለፉና ያሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲመዘገቡና የንግግር ችሎታ መለኪያ ፈተና እንዲወስዱ በሚል ባወጣው ማስታወቂያ ከ20 የማይበልጡ ባለሙያዎች ተመዝግበው ፈተና ከወሰዱ በኋላ 10 ባለሙያዎች መመረጣቸውን አስታውቋል።
በዚህ መሠረት ኤልመዲን መሃመድ፣ ኤልሻዳይ ፣ ዕድሉ ደረጄ፣ ኢሳያስ ግርማይ፣ አብዱልከሪም ሀሰን፣ኤፍሬም ወንድወሰን ፣ተስፋዬ ጸጋዬ፣ አሉላ ግርማ፣ ቢኒያም ሀይሌና ጥላሁን መንገሻ ለትንተና የተሰጠውን ፈተና አልፈው ከ17ኛው ሳምንት ጀምሮ ላለው ውድድር መመረጣቸው ማህበሩ አስታውቋል።