መነሻ ገጽ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያስጠናዉ እና በእግርኳሳችን ላይ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ እና ዘርፈ ብዙ የግምገማ ጥናት እና ልማት ፍኖተ ካርታ በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉ ጥናት ለሁለት ቀናት ያክል በርካታ የዕግርኳሱ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተከናዉኗል።
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያስጠናዉ እና በእግርኳሳችን ላይ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ እና ዘርፈ ብዙ የግምገማ ጥናት እና ልማት ፍኖተ ካርታ በሚል ርዕስ የተዘጋጀዉ ጥናት ለሁለት ቀናት ያክል በርካታ የዕግርኳሱ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተከናዉኗል።

አጋራ
አጋራ

 

የክለብ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያን በተመለከተ በተለይም በመስፈርት ደረጃ ክለቦች እንዲያሟሉ ከሚጠበቁባቸዉ መካከል:-

– የታዳጊዎች ቡድን ተሳትፎ
– የተጫዋቾች የሕክምና እና እንክብካቤ
– የታዳጊዎች ልማት ፕሮግራም
– የተጫዋቾች ምዝገባ
– የተጫዋቾች ቡድን አወቃቀር የመሳሰሉ መስፈርቶች በጥልቀት ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድርጅታዊ እሴቶች በሚል የሊጉ አስተዳደርን በሚመለከት በጥናቱ ከተዳሰሱት ሁለት ቁልፍ እና አበይት አስተዳደራዊ ምሶሶዎች መካከል አበይት ሁነዉ በርካታ ጉዳዮች ተነስተዉበታል።

የተጫዋቾች ክፍያ አስተዳደርን በተመለከተ በተለይም ደግሞ በጥልቀት በተለያዩ አለም ያሉ የስፖርቱ አመራር አካላት ባለፉት አስርት አመታት እና ሁለት አስርት አመታት ከጊዜያዊ የሜዳ ላይ ድል የዘለቀ ቀጣይነት ያለዉ እና መረጋጋት የሰፈነበት የፋይናንስ አስተዳደር ለማስፈን ይበጃል የተባሉ ዘዴዎች በስፋት ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

የክለቦች ባለቤትነት ይዞታን በተመለከተ የሀገራት ተሞክሮ ፣ የባለድርሻ አካላትን ዕይታ ፣ የአፍሪካ እግርኳስ ክለባት የባለቤትነት ይዞታ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግርኳስ እና ነህግ ማዕቀፍ በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ዉይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም በተለይ ደግሞ የተጫዋቾች ክፍያ አስተዳደር በዋናዉ ጥናት ነጥረዉ ከወጡ ትኩረት ከሚሹ አሳሳቢ ጉዳዮች መካከል አንዱ በመሆኑ ምክንያት በስፋት የባለ ድርሻ አካላት እይታ የአገራት ተሞክሮ እና ገዢ የህግ ማዕቀፍ ተቀናብረዉ ቀርበዉ ምክረ ሀሳብ እና ዉይይት ተደርጎባቸዋልም።

ለሁለት ቀናት ዉይይት የተደረገበት ጥናትም በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ዉስጥ በመፅሀፍ መልክ ታትሞ ለእግርኳስ ቤተሰቡ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...