መነሻ ገጽ Betaking Ethiopia Primer League ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 10ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !
Betaking Ethiopia Primer Leagueቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 10ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎቹ !

አጋራ
አጋራ

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 10ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አራት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቁ 22 ጎሎች በ20 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። የጎሎቹ አገባብ አራት በፍፁም ቅጣት ምት ቀሪዎቹ በጨዋታ የተቆጠሩ ናቸው። በሳምንቱ 29 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ ሶስት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ህዳር 23/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች በሳምንቱ መርሃግብር ቡታቃ ሸመና(አርባምንጭ ከተማ)፣ ባዬ ገዛኸኝ (ሀዲያ ሆሳዕና) እና አምሳሉ ጥላሁን(ፋሲል ከነማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ሲወሰን እንዲሁም ባዬ ገዛኸኝ ከጨዋታ ሜዳ በተወገደበት ወቅት የዕለቱን ዳኛ አፀያፊ ስድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት የቀረበበት በመሆኑ ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት ከተቀጣው ቅጣት በተጨማሪ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3/ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000/ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

በክለቦች ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ሲወሰን ድሬዳዋ ከተማ ክለቡ ከ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛንና የተቃራኒ ቡድን ተጫዋች አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት የቀረበባቸው ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

እሁድ ህዳር 27/2015 ዓ.ም የሚካሄደው የሁለተኛ ሳምንት የወላይታ ድቻ እና የፋሲል ከነማ ተስተካካይ ጨዋታን በተመለከተ ጨዋታው ከ10 ወደ 12፡00 ሰዓት ተለውጧል። በተጨማሪነትም ፋሲል ከነማ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን 30ኛ ሳምንት በነበረ ቅጣት የሊጉ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን ያለ ደጋፊ እንደሚካሄድ የተላለፈው ውሳኔ በእንግዳ ቡድኑ(በፋሲል ከነማ) በኩል ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልፇል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...