መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንየው ካሳሁን የሰባት ጨዋታዎች ቅጣት ተላልፎበታል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

እንየው ካሳሁን የሰባት ጨዋታዎች ቅጣት ተላልፎበታል

አጋራ
አጋራ

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 4ኛ ሳምንት በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ስድስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሁለት ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ 18 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል።

በሳምንቱ 46 ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች በቢጫ ካርድ ሲገሰፁ አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ጥቅምት 12/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በተጫዋቾች ደረጃ እንየው ካሳሁን(ድሬደዋ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ ስለተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ እንዲሁም የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋች ላይ ስለ መትፋቱ ሪፖርት ስለቀረበበት በተጨማሪ ጥፋቱ ከአንዱ ጨዋታ ሌላ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 6/ስድስት/ ጨዋታ እንዲታገድና ብር 3000 /ሶስት ሺህ / እንዲከፍል ሲወሰን ሄኖክ አየለ(ኢትዮ ኤሌክትሪክ) በጨዋታ ወቅት ሃይማኖታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ጽሁፍ የተጻፈበት ልብስ ከማሊያው ስር ደርቦ ስለመልበሱ ሪፖርት ተደርጎበት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ተጫዋቹ ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ተወስኗል፡፡

በክለቦች ደረጃ ሃዋሳ ከተማ ፣ ድሬደዋ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ባደረጉት የሳምንቱ ጨዋታ የክለባቸው የተለያዩ ከአምስት በላይ ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት እያንዳንዳቸው የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍሉ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች አፀያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው፣ ያልተገባ መልዕክት ስለማስተላለፋቸው፣ አንድ የክለቡ መለያ የለበሰ ደጋፊ በጨዋታ ወቅት ወደሜዳ ዘሎ በመግባት ሁከት ስለማስነሳቱ ሪፖርት የተደረገ በመሆኑም ደጋፊዎቹ አፀያፊ ስድብ በመሳደባቸውና ያልተገባ መልዕክት በማስተላለፋቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲሁም የክለቡ ደጋፊ ወደሜዳ ዘሎ በመግባት ሁከትና ረብሻ በማስነሳቱ በዚሁ መመሪያ መሰረት ብር 25000 /ሃያአምስት ሺህ / በድምሩ ብር 75 000 /ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ወስኗል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...