የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሴቶች ቡድን ሉሲዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸዉን ከቡሩንዲ ብሄራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ያካሂዳሉ።
ሉሲዎቹ ከብሩንዲ አቻቸዉ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸዉን ዓርብ መስከረም 11 እንዲሁም የመልስ ጨዋታቸዉን ደግሞ ማክሰኞ መስከረም 15 በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የብሩንዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ በፊት ባደረጉት ዉይይት የደርሶ መልሱ ጨዋታም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ከስምምነት እንደደረሱ የሚታወስ ነዉ።