የሴካፋየመእርጫ ጠቅላላ ጉባኤ በዛንዚባር ሆቴል ቨርድ የአባል ሀገራት እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
በጉባኤው ላይ በተደረገው ምርጫ የታንዛንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዋላስ ካይራ በድጋሚ በፕሬዝዳንትነት ሲመረጡ በተመሳሳይ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የነበሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በድጋሚ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሴካፋ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።