በአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው እየተመሩ በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሴካፋ ዞን የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ዉድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንስቶቹ የፍፃሜ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ።
እንስቶቹ ከቀናት በፊት የኬኒያዉን ቬጋ ኩዊንስን ሎዛ አበራ እና አረጋሽ ካልሳ አከታትለዉ ባስቆጠሯቸዉ ጎሎች 2-1 በሆነ ዉጤት አሸንፈዉ ለዋንጫ ማለፋቸው የሚታወስ ነዉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለፍፃሜ ጨዋታ ሲያልፍ በታሪኩ ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰአት ከታንዛኒያዉ ጄ.ኬ.ቲ ኩዊንስ ጋር በፉፋ ቴክኒካል ሴንተር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።