በመጪው ጳጉሜ 4 በካይሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል ።
በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሮይ ቪቶሪያ የሚመራው የፈርኦኖቹ ስብስብ የሊቨርፑሉን መሐመድ ሳላንም በቡድኑ አካቷል ።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም በመጪው ነሐሴ 29 ሰኞ ወደ ካምፕ በመግባት ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ ።
- ማሰታውቂያ -
ብሔራዊ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በተጨማሪም ከቀናት በኋላ ከቱኒዚያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል ።