By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
Share
Notification Show More
Latest News
የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ባህርዳር ከተማ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….
አትሌቲክስ ዜናዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ወላይታ ድቻ ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ ድሬዳዋ ከተማ
የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ
ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ለቅዳሜ የተጠራው የአ/አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠ/ጉባኤ እያወዛገበ ነው ….
ዜናዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ኢትዮጵያ ቡና እና አዳማ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 7 months ago
Share
SHARE

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሀያ ሁለተኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን ሁለት አቻ በሆነ ዉጤት አጠናቀዋል።

ሁለቱም ቡድኖች በ21ኛው ሳምንት ድል ያደረጉበትን ምርጥ አስራአንድ ሳይለውጡ ወደ ጨዋታው ገብተዋል ።

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ የተደረገው ጨዋታ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴውም እጅግ ሳቢ እና ለመመልከት የሚያጓጓ ነበር ።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በሁለቱም በኩል ዕረፍት የለሽ የሆነ እንቅስቃሴ የነበረ ሲሆን ጥሩ ጥሩ የግብ ዕድሎችንም ያስመለከተ ነበር ።

- ማሰታውቂያ -

ልክ እንደ ቀን 9:00 ጨዋታ ሁሉ በዚህ ጨዋታም በሶስተኛው ደቂቃ ላይ ግብ ተቆጥሮል ። ግብ አስቆጣሪው ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ግብ አስቆጣሪው ተጫዋች ደግሞ መሀመድኑር ናስር ።

ከግቡ በኀላ አዳማ ከተማዎች አቻ ለመሆን በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ቡናን የኋላ ክፍል ለመፈተን ጥረቶችን አድርገዋል ። ይህ ጥረታቸውም በ21ኛው ደቂቃ ላይ ፍሬ አፍርቶላቸዋል ።

ከሰሞኑ በጥሩ ብቃቱ ላይ የሚገኘው ዮሴፍ ታረቀኝ ያቀበለውን ኳስ አድናን ረሻድ በእዝቅኤል ሞራይ መረብ ላይ አሳርፎታል ። አድናን ረሻድ ባሳለፍነው ሳምንት ጨዋታም በሲዳማ ቡና ላይ ቀዳሚውን ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል ።

በሁለቱም በኩል ግብ ያስተናገደው ጨዋታው ቶሎ ቶሎ ወደ ግብ ክልል በሚደርሱ ኳሶች ታጅቦ ሲቀጥል 37ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታውን ሶስተኛ ግብ አስተናግዷል ።

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ቡና አማካይ መስዑድ መሐመድ ላይ ጥፋት መሰራቱን ተከትሎ የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት ባለ ግራ ዕግሩ ደስታ ዮሐንስ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

በሁለተኛዉ ኢጋማሽ ተሻሽለዉ የተመለሱት እና ተደጋጋሚ የግብ ዕድል መፍጠር የቻሉት ቡናማዎቹ በጨዋታዉ 63ተኛ ደቂቃ ላይ ግብ ማሰቆጠረ ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ሮቤል ተክለሚካኤል በቀጥታ ለፊት መስመር አጥቂዉ አንተነህ ተፈራ ያቀበለዉን ኳስ አጥቂው በጥሩ ቅልጥፍና ወደ ግብነት ቢቀይርም የዕለቱ መስመር ዳኛ ከጨዋታ ዉጭ በሚል ግቧ ሳትፀድቅ ቀርታለች።

በተጨማሪም ከኢትዮጵያ ቡና የቀኝ የማጥቃት በኩል የተሻማዉን ኳስ የአዳማ ከተማ ተከላካዮች በሚገባ ባለማፅዳታቸዉ ምክንያት አጥቂዉ ብሩክ በየነ ኳሷን ለመቆጣጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂዉ ሰይድ ሀብታሙ እንደምንም ተወርውሮ ኳሷን ተቆጣጥሯታል።

ምንም እንኳን ጨዋታዉን በመምራት ላይ ቢገኙም በሁለተኛዉ አጋማሽም ጥሩ ጥሩ የሚባሉ የግብ ዕድሎችን መፍጠር የቻሉት አዳማዎች በ74ተኛዉ ደቂቃ ላይ ጥሩ የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ ችለዉ ነበር ፤ በዚህም ተቀይሮ የገባዉ ነቢል ያቀበለዉን ኳስ የመስመር አጥቂዉ ቢኒያም አይተን በቀጥታ ወደ ግብ ቢልክም ኳሷ ኢላማዋን ሳትጠብቅ ወደ ዉጭ ወጥታለች።

ከዚች ሙከራ ከአንድ ደቂቃ በኋላም በድጋሚ ቢኒያም አይተን ከሳጥኑ ጠርዝ ላይ ጥሩ ዕድል አጊኝቶ በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክሩም ግብ ጠባቂዉ በቀላሉ ኳሷን ተቆጣጥሯታል።

በ78ተኛዉ ደቂቃ ላይ ሀይለሚካኤል አደፍርስ ከኢትዮጵያ ቡና የግራ ማጥቃት በኩል ያሻማውን ኳስ አጥቂዉ መሐመድ ኑር ናስር በአስገራሚ አክሮባቲክ ምት ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ ማድረግ ችሏል።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይ ለመሸናነፍ በሁለቱም በከል የነበሩት ጥረቶች ውጤታማ ሳይሆኑ አንድ አንድ ነጥብ ይዘው ከሜዳ ወጥተዋል ።

በ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሚያዝያ 30(ሰኞ) በ9:00 አዳማ ከተማ ወላይታ ድቻን ሲገጥም በተከታዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከባህርዳር ከተማ ይጫወታል ።

You Might Also Like

የጨዋታ ዘገባ | ባህርዳር ከተማ ከአራት ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቅዳሜውን ጠቅላላ ጉባኤን አገደ….

የጨዋታ ዘገባ | የስድስተኛ ሳምንት ቀዳሚ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ

ለቅዳሜ የተጠራው የአ/አ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠ/ጉባኤ እያወዛገበ ነው ….

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የጨዋታ ዘገባ | የጣና ሞገዶቹ በተከታታይ ጨዋታዎች ነጥብ ጥለዋል
Next Article የጨዋታ ዘገባ | መቻል ወደ አሸናፊነት ተመልሷል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀዋሳ ከተማሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የአምስተኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ግብ ሳይስተናገድበት ተጠናቋል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 2 years ago
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ በቀጥታ /LIVESCORE/ ይከታተሉ።
ፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ አስፈርመዋል!
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ለግ 11ኛ ሳምንት /LIVESCORE/
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?