By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የጨዋታ ዘገባ | የዓብስራ ተስፋዬ አስደናቂ ግብ የጣና ሞገዶቹን አሸናፊ አድርጓል
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችሀዋሳ ከተማባህርዳር ከተማየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | የዓብስራ ተስፋዬ አስደናቂ ግብ የጣና ሞገዶቹን አሸናፊ አድርጓል

Habtamu Mitku
Habtamu Mitku 3 years ago
Share
SHARE

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ29ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን 1 – 0 አሸንፏል ።

በጨዋታው በባህርዳር ከተማ በኩል በ28ኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና 4 – 0 በተረቱበት ጨዋታ ላይ ከተጠቀሙት አሰላለፍ አራት ለውጦች በማድረግ በተስፋዬ ታምራት ፣ አለልኝ አዘነ ፣ ቻርለስ ሪባኑ እና ሀብታሙ ታደሰ ምትክ ፈቱዲን ጀማል ፣ ፉአድ ፈረጃ ፣ ፍቅረሚካኤል አለሙን እና አደም አባስን ተክተው ሲገቡ በሀዋሳ ከተማ በኩል ኢትዮ ኤሌክትሪክን በረቱበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ ሰዒድ ሀሰንን በዳንኤል ደርቤ ተክተው ጨዋታውን መጀመር ችለዋል ።

በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ በኳስ ቁጥጥሩ ተሽለው የታዩ የመሰሉት ሀዋሳ ከተማዎች ቢመስሉም ቀስ በቀስ ጨዋታው ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ እስከ መጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ድረስ አስመልክቶናል ።

- ማሰታውቂያ -

በአጋማሹ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ደርሶ ጥሩ የግብ ዕድሎች በመፍጠር የተሻሉ የነበሩት የጣና ሞገዶቹ በተደጋጋሚ አላዛር ማርቆስን የፈተኑ ሙከራዎችን ማድረግ ችለው ነበር ።

በሀዋሳ ከተማ በኩል የነበሩት የማጥቃት እንቅስቃሴዎች በተጋጣሚያቸው የኋላ ክፍል በቀላሉ ይነጠቁ ነበር ።

የጨዋታው ቀዳሚ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ በ9ኛው ደቂቃ ላይ የተደረገ ሲሆን መድኃኔ ብርሀኔ ከግራ መስመር ወደ ግብ ያሻማውን ኳስ ሙጂብ ቃሲም በግንባር ገጭቶ ወደ ግብ ቢልከውም በታፔ አላዝየር ተመልሷል ።

ከሶስት ደቂቃዎች በኋላም በሀዋሳ ከተማ በኩል አሊ ሱሌማን ከሳጥኑ ርቆ የወጣውን ግብ ጠባቂውን ፔፔ አላዝየርን አልፎ የነበረ ቢሆንም ፈቱዲን ጀማል ኳሱን ግብ ከመሆን አድኖታል ።

በባህርዳር ከተማ በኩል ማማዱ ሲዲቤ በ13ኛው ደቂቃ ላይ የቡድኑን ቀዳሚ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ሲያደርግ በ15 እና 22ኛው ደቂቃ ላይ ፉአድ ፈረጃ እና ያብስራ ተስፋዬ ከቅጣት ምት በቀጥታ ወደግብ የመቷቸው ኳሶች በግብ ጠባቂው ተመልሰዋል ።

የጣና ሞገዶቹ ተደጋጋሚ የግብ ዕድሎች እየፈጠሩ በቀጠሉበት ደቂቃዎች ላይ ማማዱ ሲዲቤ ጥሩ አጋጣሚን አግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

አጥቂው ከረጅም ርቀት የተላከለትነ ኳስ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ከፍ አድርጎ ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል ።

ሀዋሳ ከተማዎች የአጋማሹ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ በኳስ ቁጥጥሩ የተሻሉ መስለው ቢታዩም የግብ ሙከራዎችን ከማድረግ አንፃር ግን ደካማ እንቅስቃሴን ነበርን ሲያሳዩ የነበሩት ።

የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ በተጨማሪ ደቂቃ ላይ ያብስራ ተስፋዬ ያስቆጠረው አስደናቂ ግብ ቡድኑን በ1 – 0 መሪነት ወደ እረፍት እንዲያመራ አስችሎታል ።

ማማዱ ሲዲቤ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው አላዛር ማርቆስ ሲመልሰው ከሳጥን ውጪ ሆኖ ያገኘው 8 ቁጥር ለባሹ ያብስራ በግሩም ሁኔታ አስቆጥሮታል ።

የሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሀይቆቹ የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ሀይቆቹ ተደጋጋሚ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች በማድረግ ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን አድርገዋል ።

በ49 እና 52ኛው ደቂቃ ላይ ሰዒድ ሀሰን በግንባር ገጭቶ ለማስቆጠር ያደረጓቸው ጥረቶች ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል ።

በ53ኛው ደቂቃ ላይም ሙጂብ ቃሲም ከሳጥን ውጪ ያደረገው የግብ ሙከራ በታፔ አላዝየር ተመልሷል ።

ሀይቆቹ ጫናቸውን አጠናክረው በመቀጠል የአቻነቱን ግብ ለማግኘት ቢጥሩም በጥሩ ንቃት ላይ የነበረው የባህርዳር ከተማ የኋላ መስመር ይህን የሚፈቅድ አልነበረም ። በ69ኛው ደቂቃ ላይ የመሀል ተከላካያቸው የሆነው በረከት ሳሙኤል በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ ተሰናብቷል ።

በቀጣዮቹ ደቂቃዎች ላይም በይበልጥ የጣና ሞገዶቹ የማጥቃት እንቅስቃሴ የታየበት ነበር ። በ71ኛው ደቂቃ ላይ ፍፁም ጥላሁን ከተከላካዮች ጀርባ የተጣለለትን ኳስ አግኝቶ አስቆጠረው ተብሎ ሲጠበቅ ሳይጠቀምበት ቀርቷል ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ፍራኦል መንግስቱ ከግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ወደ ግብ መምታት ችሎ የነበረ ቢሆንም አላዛር ማርቆስ ኳሱን ግብ ከመሆን አድኖታል ።

የጣና ሞገዶቹ በተደጋጋሚ በቀኝ መስመር በኩል ወደ ሀዋሳ ከተማ ሳጥን መግባት ቢችሉም አጋጣሚዎችን ሳይጠቀሙባቸው ቀርተዋል ።

በ85ኛው ደቂቃ ላይም ይሄነው የማታ ከፍቅረሚካኤል አለሙ ተቀብሎ ወደ ግብ የመታው ኳስ በግብ ጠባቂው ተመልሷል ።

በመጨረሻም ጨዋታው በባህርዳር ከተማ የ1 – 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Habtamu Mitku
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የጨዋታ ዘገባ |ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረዉ የሊጉ ሻምፒዮን መሆን የቻለበትን ዉጤት አስመዝግቧል !!
Next Article የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎችዜናዎችኢትዮ-ኤሌክትሪክ

ኢትዮ ኤሌትሪክ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል !!

Ermias Misganaw By Ermias Misganaw 3 years ago
አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።
ሪፖርት | መከላከያ ኢትዮ-ኤሌክትሪክን በማሸነፍ የሊጉን ሁለተኛ ዙር በድል ጀምሯል።
በኮቪድ 19 የተያዙት 5 ተጨዋቾች በድጋሚ ሳይመረመሩ ቀሩ
ትግራይ ዋንጫ ከጥቅምት 30-ህዳር 9 በመቐለ ይካሄዳል
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?